2009-11-23 15:24:54

ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የክርስቶስ ስቃይ ተካፋይ


እ.ኤ.አ. በ 1997 ዓ.ም. በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት የወደመው የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ባሲሊካ የላይኛው ክፍል ዳግም የተገነባበት እና የታደሰበት ቀን ምክንያት በማድረግ ትላንትና የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ የመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ መቅረቡ ተገለጠ።

በቀረበው መሥዋዕተ ቅዳሴ ይህ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ባሲሊካ መቼም ቢሆን የሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት የማይሰረዝ መሆኑ በእግዚአብሔር ጥሪ እና ፈቃድ አማካኝነት የሚኖሩት የቅዱስ ፍራንቸስኮች ማህበር ወንድሞች ዳግም ለተገነባው ባሲሊካ ብቻ ሳይሆን በቅድስት ቤተ ክርስትያን የተሃድሶ ምስክሮች ናቸው ብለዋል። ብፁዕነታቸው ትላንትና እሁድ በተከበረው የክርስቶስ ንጉሥ ዓቢይ በዓል ቅዱስ ፍራንቸስኮስ በመስቀል ላይ የተመሰከረው እና በትንሳኤ የተረጋገጠው የክርስቶስ ንጉሥነት ጠንቅቆ በቃል እና በሕይወት ታምኖ በመኖር በተለይ የክርስቶስ ስቃይ ተካፋይ በመሆን ለሁሉም መስክሮታል ብለዋል።

ሁሉም የራሱን መስቀል ተሸክሞ ዓይኖቹን ወደ ክርስቶስ በማቅናት ልክ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ድኽነትን በማፍቀር በእውነተኛ ፍቅር በመዋደድ በተለይ ደግሞ ለድኾች ልዩ አክብሮት እንክብካቤ በመስጠት እምነታችንን መመስከር ይገባናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.