2009-11-18 13:47:19

በቤተ ክርስትያን እና በሓዋርያዊ አገልግሎት ያላቸው ሚና


መስማት እና መናገር ለተሳናቸው የማኅበርሰብ አባላት በተለያዩ የቤተ ክርስትያን የግብረ ሓዋርያዊ ኖልው መስክ ተገቢ ሥፍራ እንዲኖራቸው እና ለሚሰጡት አስተዋጽኦ አቢይ ትኵረት እንዲሰጠው የሚያሳስብ እዚህ በቫቲካን የጤና ጥበቃ እና የጤና ጥበቃ RealAudioMP3 ባለ ሙያዎች ጉዳይ የሚነከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያነቃቃው ዓለም አቀፋዊ ስብሰባ እ.ኤ.አ. ከህዳር 19 ቀን እስከ ህዳር 21 ቀን 2009 ዓ.ም. እንደሚካሄድ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት መግለጫ ይጠቁማል።

ይህ ነገ ስለ ሚከፈተው ጉባኤ በተመለከተ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዞሞውስኪ እና መናገር እና መስማት ለተሳናቸው ሓዋርያዊ አገልግሎት የሚሰጠው የንኡሳን ልኡካን ማህበር ኣባል ኣባ ሳቪኖ ካስቲሊዮኔ በጋራ ጋዜጣዊ መገልጫ ሲሰጡ፣ በዓለማችን መስማት እና መናገር የተሳናቸው 278 ሚሊዮን ሕብዝ እና ከነዚህ ውስጥ መስማት እና መናገር ለተሳናቸው የሚገባ የሕክምና አገልግሎት እምብዛም የማያገኙት 80% በመቶ በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች እንደሚኖሩ በመግለጥ፣ ተገቢ ሕክምና ካለ ማግኘት አንጻር ያጋጠማቸው ያለ መስማት እና ያለ መናገር ችግር ሊፈወስ የሚቻል ሆኖ እያለ መፍትሔ የሌለው ሆኖ ይቀራል፣ በዚህ ባጋጠማቸው ችግር ምክንያትም ከማህበራዊ ጉዳይም ሆነ ከሥራ ዓለም ተገለው ለከፋው ድኽነት ተጋልጠው እንዲኖሩ መገደዳቸውም ብፁዕ ኣቡነ ዞሞውስኪ ገልጠው፣ ቤተ ክርስትያን ለነዚህ የህብረተሰብ አባላት መንፈሳዊ እንክብካቤ እንዲሁም ሰብአዊ እና ማህበራዊ ብሎም ሙያዊ ሕንጸተ በማቅረብ በሚኖሩበት ማኅበረሰብ እና ቤተ ክርስትያን ተገቢ ሥፍራ እንዲኖራቸው በትክክል ለነርሱ ያቀና ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እቅድ እንዳላት አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.