2009-11-16 13:58:16

ቫቲካን፣ ስደተኛነት በዓለማዊ ትሥሥር መስፋፋት ዘመን


ስደት የማኅበራዊ የሰብአዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳይ የሚያስከትለው ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለው ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ክስተት ሲሆን፣ በተለይ ዓለማዊ ትሥሥር እጅግ እየተስፋፋ ባለበት ዘመን ስደት ሁሉንም RealAudioMP3 አገሮች የሚመለከት ክስተት መሆኑ በማረጋገጥ፣ እዚህ በቫቲካን የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያነቃቃው እ.ኤ.አ. ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. የተጠናቀቀው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ አመርቂ እንደነበር ተገልጠዋል።

ይህ ባለፈው ሓሙስ የተፈጸመው ስደት በዓለማዊ ትሥሥር መስፋፋት በሚል ርእሰ ጉዳይ የተመራው ዓለም አቀፋዊው ስብሰባ፣ የዛሬ ዓመስት ዓመት በፊት የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Erga Migrantes Caritas Christi”-የክርስቶስ ፍቅር ለስደተኞች በሚል ርእሰ ጉዳይ ያወጣው መመሪያ የገመገመ መሆኑ ሲገለጥ፣ ዓለማዊ ትሥሥር እጅግ በጎላበት ወቅታዊው ዘመን፣ ለስደተኛ እና ለተፈናቃይ ህብዝ የሚሰጠው አገልግሎት በመቃኘት፣ ስደተኛ ሃብት እንጂ ችግር አለ መሆኑ ጉባኤው አስምሮበታል።

የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ በዚህ ዓለማዊ ትሥሥር እጅግ በጎላበት ዘመን ስደተኛ እና ተፈናቃይ ያለማችን ህዝብ በተስተናገደበት አገር ተዋህዶ እና ተቀባይነት አግኝቶ መብቱን እና ግዴታውን አውቆ እንዲኖር የሚከናወነው ሂደት ጠለቅ አድርጎ የተወያየ ስብሰባ መሆኑ እና ለሰላማዊ ማኅበራዊ ሕይወት መሠረት ሁሉም በመከባበር የተፈጥሮ ሃብት በእኵል ተጠቃሚ ሲሆን ብቻ መሆኑ የተካሄደው ስብሰባ እንዳሰመረበት ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.