2009-11-16 14:03:54

በካህን ተልእኮ የግኑኝነት ሚና


እዚህ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ የስነ መገናኛ ብዙሃን የትምህርት ዘርፍ ያነቃቃው በክህነ ተልእኮ የግኑኝነት ሚና በሚል ርእስ የተመራ ዓውደ ጥናት እፊታችን ረቡዕ ህዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. እንደሚጀመር RealAudioMP3 ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

እያንዳንዱ ካህን ክርስቶስን የሚወክል በመሆኑ እና ከጥሪውም አንጻር ከሌሎች ጋር የሚገናኝ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያሰማ የሚመሰክር ቅዱሳት ሚስጢራትን በመሥራት ከሌሎች ጋር የሚገኝ በራሱ የሚዘጋ ሳይሆን ወደ ሌሎች ያቀና ከሌሎች ጋር የሚገናኝ ሲሆን፣ ይህ የሚካሄደው ዓውደ ጥናት ይኸንን እና በተለይ ደግሞ ዘንድሮ በመታሰብ ላይ ያለው የክህነት ዓመት እግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ዜኒት የዜና አገልግሎት በማመልከት በዓውደ ጥናቱ የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንዛ የመገናኛ ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፖውል ቲገ እንደሚሳተፉም የዜና አግልግሎቱ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.