2009-11-13 13:32:25

ጸረ ሰው ፈንጅ


ከምድረ ገጽ ጨርሶ አደገኛው ጸረ ሰው ፈንጅ ምርት እገዳ የተደረሰው በኦታዋ የሚጠራው ውል አወንታዊ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ በ 2009 ዓ.ም ስለ ተቀባሪ ጸረ ሰው ፍፈንጅ ጉዳይ በተመለከተ በጀነቨ ይፋ RealAudioMP3 የወጣው ሰነድ ይጠቁማል።

ሰነዱን ያመላከተው ሚስና የዜና አገልግሎት፣ በዓለማችን በተለያዩ ውጥረቶች ምክንያት የተቀበሩት ጸረ ሰው ፈንጅ ለማክሸፍ የሚደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ሲታወቅ፣ 3200 ኪሎ ሜትር ስኵየር መሬት ፈንጅ ተቀብሮበት የነበረው ክልል ከፈንጅ ነጻ ሲሆን፣ በ 2008 ዓ.ም. በተቀበረው ጸረ ሰው ፈንጆ ሳቢያ 5,197 ሰዎች ለሞት አደጋ መጋለጣቸው ለማውቅ ተችለዋል፣ ይህ በጄነቭ ይፋ የሆነው ሰነድ፣ ዓለማችን ከዚህ አደገኛው ጸረ ሰው ፈንጅ ነጻ የማድረጉ ጥረት አወንታዊ ውጤት እያስገኘ ነው፣ ሆኖም ግን ገና ብዙ ጥረት ማድረግ እንደሚጠይቅ በማሳሰብ አሁንም አንዳንድ አገሮች አነርሱም የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ቻይና ህንድ ፓኪስታን እና ሩሲያ የኦታዋ ውል ባይፈርሙበትም ውሉ በመደገፍ የሚሰጡት አስተዋጽኦ የሚመሰገን መሆኑ ሰነዱን የጠቀሰው ሚስና የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.