2009-11-13 13:29:20

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት 60ኛው ይፋዊ ጉባኤ


በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ ሲካሄድ የስነበተው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት 60ኛው ይፋዊው ጉባኤ ትላትና የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ባሰሙት ንግግር ተጠናቋል። RealAudioMP3

ብፁዕነታቸው በጉባኤው ፍጻሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቅዱስ አባታችን ለጉባኤው ባስተላለፍት መልእክት ተደገፎ እና በጸሎት ኅብረቱን በመመስከር የተለያዩ የኢጣሊያ ቤተ ክርስትያን እና እንዲሁም የኢጣሊያው ፖሊቲካዊ ማኅበራዊ እና ኤክኖሚያዊ ነክ የሆኑትን አንገብጋቢ ጥያቄዎች በቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ትምህርት ጉዳይ ሥር በመዳሰስ መከናወኑ በማብራራት፣ በኢጣልያ የሚታየው ፖለቲካዊ ሽኩቻ እና ውጥረት ተወግዶ ለአገር እና ለሕዝብ ጥቅም ያቀና ኃላፊነት የተካነው ፖሊቲካዊ ውይይት ማረጋገጥ እጅግ አንገብጋቢ መሆኑ የብፁዕን ጳጳሳት ምክር ቤት እንዳሰመረበት ገልጠዋል። አክለውም በዚህ ሞትን የሚፈራ ነገር ግን ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ለማክበር ግድ የማይል የሞት ሓቅ የሚሸሽ ባህል በስፋት ውይይት ተደርጎበት፣ የሕይወት ባህርያዊ ለውጠ ክስተት ለመቆጣጠር በተለይ ደግሞ የእድሜ መግፋት ሂደት ለመቆጣጠር ባይቻልም የእድሜ መግፋት መግለጫዎችን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት በሰዎች ዘንድ እያስከተለው ያለው የሕይወት ፍጻሜ የማግለሉ ባህል ተገቢ ምላሽ ለመስጠት የኢጣሊያ ቤተ ክርስትያን አዲስ መጽሓፈ ግንዘት ማቅረቧ ገልጠዋል።

በመጨረሻም በቅርቡ የኤውሮጳው የስብአዊ መብት እና ፈቃድ ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ፍርድ ቤት በማህበራዊ የአገልግሎት መስጫ መዋቅሮች መስቀል እንዳይሰቀል ያስተላለፈው ፍርድ በመጥቀስ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተጨባጭነት የሌለው ፖለቲካዊ ርእዮት ተገን ያደረገ የኢጣሊያን ባህል የማያውቅ ውሳኔ ነው ካሉ በኋላ፣ የመገናኛ ብዙሃን የሕንጸት መሳሪያ ሕሊናን የሚያነቃቁ መሆን ይገባቸውል ብለዋል። የሚከሰቱት ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ውጥረቶች ለማስወገድ ለአዲሱ ትውልድ በግብረ ገብ እና በስነ ምግባር ማነጽ ወሳኝ ነው፣ ለማኅበራዊ ሰላም መሠረት ወጣቱን ትውልድ ማነጽ የሚለው እቅድ ገቢራዊ መሆን አለበት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.