2009-11-11 14:41:30

የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ የሚነካበከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት


እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በኩባ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ትውስት የኩባ ሕዝብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚሕች አገር ሓዋርያዊ ጉብኝት ያካሂዱ ዘንድ RealAudioMP3 አቢይ ጉጉት እንዳላቸው በኩባ የአራት ቀን ሓዋርያዊ ጉብኝታቸውን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኙት የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ የሚንከባከብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ቀርበው በመገንዘብ፣ አንድ የኤፈ እለታዊ ጋዜጣ ጋዜጠኛ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኩባ ሓዋርያዊ ጉብኝት ባጭር ጊዜ ውስጥ ገቢራዊ ይሆናል ወይ ሲል ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ነቢይ እኳ ባልሆን ይኸ ጉጉት ገቢራዊ ሆኖ ማየቱ እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ከኩባ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር መገናኘታቸውም ሲገለጥ፣ የኩባው ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ቤተ ክርስትያን መገናኛ ብዙሃን እና የስነ ቅመራ ባህል በሚል ርእስ እያካሄደው ባለው ይፋዊ ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ መሆናቸውም ሲነገር፣ ከተለያዩ በኩባ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ ሠራተኞች እና ጋዜጠኞች ጋር ጭምር ተገናኝተዋል።

የላቲን አሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን በጠቅላላ የብፁዕ አቡነ ቸሊ የኩባ ሓዋርያዊው ጉብኝት በተመለከተ ሰፊ ሓተታ ማቅረባቸው ሲነገር፣ የኩባ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በኩባ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ተስታፊነቷ ተረጋግጦ እና ጉልህ ሚና ይኖራት ዘንድ የኩባ ብፁዓን ጳጳሳት ፍላጎት ለኩባ መንግሥት በተለይ ደግሞ የኩባ የመገናኛ እና የማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒ. ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት ማቅረባቸው ገልጠው፣ መልሱ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው አስታውቀው፣ በመገናኛ ብዙሃን ረገድ የኩባ ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ለኩባ ህዝብ እሴቶችን መልእክቶቿንና የእግዚአብሔርን ቃል ለማቅረብ ህዝቡን ለማነጽ የሚያስችላት መድረክ ነው እንዳሉም አንሳ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.