2009-11-09 13:59:04

ቫቲካን፣ ስደተኛነት በዓለማዊ ትሥሥር መስፋፋት ዘመን


ስደት የማኅበራዊ የሰብአዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳይ የሚያስከትለው ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ክስተት ሲሆን፣ በተለይ ዓለማዊ ትሥሥር እጅግ እየተስፋፋ ባለበት ዘመን ስደት ሁሉንም አገሮች RealAudioMP3 የሚመለከት ክስተት መሆኑ በማረጋገጥ፣ እዚህ በቫቲካን የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልው የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያነቃቃው እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 12 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚካሄደው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ዛሬ በይፋ መጀመሩ ከቅድስት መንበር የተሰራጨ ዜና ያረጋገጣል።

ስደት በዓለማዊ ትሥሥር መስፋፋት በሚል ርእሰ ጉዳይ የተመራው ዓለም አቀፋዊው ስብሰባ የዛሬ ዓመስት ዓመት በፊት የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Erga Migrantes Caritas Christi”-የክርስቶስ ፍቅር ለስደተኞች በሚል ርእሰ ጉዳይ ያወጣው መመሪያ መለስ ብሎ በመቃኘት በነዚህ ባለፉት ዓምስት ዓመታት ለስደተኞች እና ለተፈናቋዮች እንዲሁም ለተጓዦች የተሰጠው ሓዋርያዊ አገልግሎት በመገምገም የሚከናወን መሆኑ ይህ ሰብአዊ ክስተት በተመለከተ የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ ከቫቲካን ረዲዮ ቫቲካን ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በመግለጥ፣ ዓለማዊ ትሥሥር እጅግ በጎላበት ወቅታዊው ዘመን ለስደተኛ እና ለተፈናቃይ ህብዝ የሚሰጠው አገልግሎት አወንታዊው እና አሉታዊው ገጽታውን እንዲሁም፣ ዓለም አቀፍ የስደተኛ እና የተፈናቃይ ጉዳይ የሚመለከተውን መመሪያ በመዳሰስ ስደተኛ ትልቅ ሃብት መሆኑ የሚያጎላ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ነው ብለዋል።

የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ በዚህ ዓለማዊ ትሥሥር እጅግ በጎላበት ዘመን ስደተኛ እና ተፈናቃይ ያለማችን ህዝብ በተስተናገደበት አገር ተዋህዶ እና ተቀባይነት አግኝቶ መብቱን እና ግዴታውን አውቅ እንዲኖር የሚከናወነው ሂደት ጠለቅ አድርጎ የሚያጤን ስብሰባ ነው በማለት፣ ለሰላማዊ ማኅበራዊ ሕይውት መሠረት ሁሉም በመከባበር የተፈጥሮ ሃብት በእኵል ተጠቃሚ ሲሆን ብቻ ነው ብለዋል።

ይህ ዛሬ በቫቲካን የተጀመረው ዓለም አቀፋዊው ስብሰባ ከሚወያይባቸው ርእሶች አንዱ፣ በእስያ በላቲን አሜሪካ እና በአፍሪቃ በጠቅላላ በዓለማችን ስላለው የስደተኛው እና የተፈናቃዩ ሁኔታ የሚመለከት መሆኑ ብፁዕ ኣቡነ ማርኬቶ ጠቅሰው፣ የታን ፎ ሆ ቺ ሚን ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ዣን ባፕቲስት ፋም ሚህን ማን፣ በእስያ እየተረጋገጠ ያለው በርህን መክፈት የሚለው የስደተኛ እና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚመለከተው ፖለቲካ ርእስ በማድረግ ንግግር እንደሚያደርጉ ሲገለጥ፣ በዚህ በእስያ የከተሞች መስፋፋት የቀሰቀሰው የገጠር ክልል ነዋሪ ህዝብ ጸአት በቁምስናዎች እያስከትለው ያለው ለውጥ እና ይኸንን ክስተት ቁምስናዎች እንዴት ባለ መልኩ መልስ እየስጡበት መሆናቸውም ሰፋ ባማድረግ እንደሚያብራሩ ብፁዕ ማርኬቶ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.