2009-11-09 14:02:36

ሶማሊያ


በሶማሊያ መርካ ከተማ አንድ 33 ዓመት እድሜ የነበረው ወጣት እና አንዲት ሴት በዙሙት ተከሰው በድንጋይ ተወግረው እንዲገሉ በክልሉ ያለው እስላማዊ ፍርድ ቤት መበየኑ ሲገለጥ፣ ወጣቱ ትላትና 300 ሕዝብ በተሰበሰበበት RealAudioMP3 አደባባይ ሲገደል፣ ሴቷ እርጉዝ በመሆኗ ምክንያት የተበየነባት የሞት ቅጣት ከወለደች በኋላ እንዲፈጸምባት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉ ቢቢሲ በድረገ ገጹ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

የሶማሊያ ርእሰ ብሔር ሼክ ሻሪፍ ሼክ አህመድ እስላማዊው ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ በማውገዝ በእስልምና ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው የምስልምናውን ሃይማኖትን የሚጻረር ነው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በዚሁ ክልል ሁለት ያገሪቱ ዜጎች በስለላ ወንጀል ተጠርጥረው ለክስ ከቀረቡ በኋላ ፍርድ ቤቱ ወንጀለኞች በማለት በድንጋይ ተወግረው እንዲገለሉ በይኖባቸው ለሞት መዳረጋቸው ሲንገር፣ እንዲሁም ባለፈው ዓመት አንዲት የ 13 ዓመት እድሜ የነበራት ህጻን በኪሲማዮ ባንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች የወሲብ አመጽ ደርሶባት፣ ሆኖም ግን እስላማዊው ፍርድ ቤት አመዝራለች በማለት ለሞት በይኖባት በድንጋይ ተወግራ መገደሏ የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.