2009-11-07 15:44:50

ርእሰ ኪቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከኪነ ጥበባውያን ጋር ይገንኛሉ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በዚሁ በተያዝነው ሕዳር ወር ሀያ አንድ ቀን ከኪነ ጥበባውያን ጋር እንደሚገናኙ በቅድስት መንበር የባህል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጂያን ፍራንኮ ራቫሲ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥጠዋል ።

ቅድስቲ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ከኪነ ጥበብ ጋር አዲስ ትብብር እና ግንኙነት ትሻለች ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ራቫሲ በየቫቲካን ማኅተም ክፍል ለተገኙ መገናኛ ብዙኀን መግለጣቸው መግለጨው ገልጸዋል ።

ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነፍሰ ሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ለኪነ ጥበባውያን ነግግር ማድረጋቸው እኤአ 1999 ደግሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዲሁ ለኪነ ጥበባውያን መልዕክት መጻፋቸው የሚታወስ ነው ።

ይህ ሕዳር ሀያ አንድ ቀን በሲስቲና ቤተ ጸሎት በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና በየዓለማችን ኪነ ጥበባውያን መካከል የሚደረገው ግንኙነት በቅድስት መንበር የባህል ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና በየቫቲካን ቤተመዘክር የተዘጋጀ እና የተቀናበረ መሆኑ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

የባህል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጂያን ፍራንኮ ራቫሲ እንንደገለጡት ለዚሁ ግንኙነት አምስት መቶ ኪነ ጥበባውያን ተጋብዘዋል እስካሁን ድረስ ሁለት መቶ ስልሳ ኪነ ጥበባውያን የይሁንታ ምላሽ ሰጥተዋል ።

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለመገናኘት የተጋበዙ ኪነ ጥበባውያን የተለያየ እምነት እና የፖሊቲካ ሥነ ሐሳብ የሚከተሉ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ካቶሊካውያን ኪነ ጥበባውያን መሆናቸው ብፁዕ አቡነ ጂያን ፍራንኮ ራቫሲ ማብራርያ መስጠጣቸው ተመልክተዋል።

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር የሚገናኙ ኪነ ጥበባውያን የስዕል የቅርጻ ቅርጽ የህንጸት የሥነ ጽሑፍ የቅኔ የሙዚቃ የሲነማ የትያትር ኪነ ጥበባውያን መሆናቸው ግንኝነቱ ያዘጋጁ እና ያቀናበሩ በቅድስት መንበር የባህል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ራቫሲ እና የቫቲካን ቤተ መዘክር ዋና ሐላፊ ፕሮፈሶር አንቶንዮ ፓኦሊቺ መግለጻቸው ተገልጸዋል ።

በዚሁ ሕዳር ወር ሀያ አንድ ቀን የሚከናወነው ግንኙነት በአጠቃላይ ኪነ ጥበብ እና የእምነት ቅዱሳን ኪነ ጥበቦች ፊት ለፊት እንደሚገናኙ ተወስተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.