2009-11-02 12:38:55

የሃንጋሪ ቤተ ክርስትያን


በሃንጋሪ የኮሙኒዝም ሥርዓት በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ሕዝበ እግዚአብሔርን ቤተ ክርስትያንን በብርታት በማገልገል እግዚአብሔርን ከመካድ የሰማዕትነት ጸጋ ለመቀበል የመረጡት እ.ኤ.አ. መጋቢት 4 ቀን 1951 ዓ.ም. RealAudioMP3 ባሰቃቂው የኮሙኒስት መንግሥት ኪስታርክሳ በሚገኘው ወህኒ ቤት በእስር እያሉ በደረሰባቸው ግርፋት ስቃይ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የእግዚአብሔር አገልጋይ ብፁዕ አቡነ ዞልታን ሜስዝለንዪ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 31 ቀን 2009 ዓ.ም. ብጽእና እንደታወጀላቸው ተገለጠ።

በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተሳተፉት የኤውሮፓ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሊቀ መንበር በሃንጋሪ የኤስተርጎም እና የቡዳፔስቲ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ ባሰሙት ስብከት፣ ብጹዕ አቡነ ዞልታን ሕዝበ እግዚአብሔርን ግልጽ በሆነው ለእምነት እና ለቤተ ክርስትያን ተአዝዞ በእለታዊ ኑሮአቸው ወንጌልን በቃል እና በሕይወት የመሰከሩ ናቸው፣ በማለት ሰውን መግለደል ይቻል ይሆናል መንፈሱ ግን ማንም ሊያጠፋት አይችልም፣ የክርስቶስ ተከታዮች ስቃይ እና መከራ ፈተና ስደት እና ለሞት አደጋም ጭምር የተጋለጡ ቢሆንም ቅሉ በነርሱ በሚኖረው ክርስቶስ አማካኝነት ሁሉን ችለው ወንጌል የሚመሰክሩ አገልጋዮች ናቸው። አንዳንድ የታሪክ ሊቃውንት ነን ባዮች ቤተ ክርስትያንን የሚያንቋሽሽ ጽሑፎች የሚበትኑ ቢሆንም ቅሉ ማንም ልኡካነ ወንጌል ወደ ኋላ ሳይል፣ እራሱን የሚሰብክ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰብክ ነው ስለዚህም ዘወትር አያፍርም አይፈራምም፣ ብፁዕ ሰማእት አቡነ ዞልታን ይኸንን ያረጋገጡ የቤተ ክርስትያን ልጅ፣ የክርስትያን አባት ነበሩ በማለት ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ ገልጠዋቸዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ወክለው የቅዳሴውን ሥነ ሥርዓት የመሩት የቅስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ አማቶ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ብጹዕ ዞልታን ሜስዝለንዪ ለሕይወት ወንጌል ለቤተ ክርስያን እና ለሓቅ ታዛዦች እንድንሆን ያነቃቃናል፣ በውህደት በፍቅር እና በነጻነት በመኖር የፍቅር የሕይወት የወንድማማችነት መንፈስ የተካነው ሥልጣኔ ለመገንባት ለመመስከር እና ለማነቃቃት ብፁዕ ዞልታን ይጋብዘናል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.