2009-11-02 17:02:46

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅድስት መንበር የተመደቡ አዲስ የቡልጋርያ አምባሳደር ተቅብለው አነጋግረዋል


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በቅድስት መንበር የተመደቡት የቡልጋርያ መንግስት አዲስ አምባሳደር ኒኮላ ካሉዶቭ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ግንኙነት እንደገለጡት ፡ ከሃያ ዓመታት በፊት የበርሊን ግድግዳ እንደወደቀ ቡልጋርያ የዲሞክራሲ ሂደት መጀመርዋ እና ከሁለት ዓመታት በፊትም የኤውሮጳ ሕብረት አባል መሆንዋ ጠቅሰው ፡ የኤውሮጳ ሃገራት ሕብረት በክርስትያናዊ እሴቶች በሰው መብት ጥበቃ እና ትብብር የተመረኮሰ መሆኑ መዘንጋት አይገባም ።

ቡልጋርያ የኤውሮጳ ሕብረት አባል ለመሆን ያካሄደችው ጥረት የሚመሰገን መሆኑ ያመለክቱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የኤውሮጳ ሕብረት ለማነጽ ብሔራዊ ባህላዊ ማንነት ምርኩስ ያደረገ መሆን እንደሚገባ መግለጻቸው የቫቲካን መግለጫ አመልክተዋል።

ቡልጋርያ ጥንታዊ የክርስትና እሴቶች ባለ ቤት መሆንዋ ያወሱት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ እሴቶቹ በግብረ ገብነት የተሸኘ ሰላማዊ ኑሮ ለመኖር እንደሚረዱ መግለጻቸው መግለጫው አመልክተዋል ።

የክርስትና እሴቶች ለሰብአዊ እና ኅብረ ተሰብአዊ ኑሮ መሠረት መሆናቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቅድስት መንበር ከተመደቡ የቡልጋርያ መንግስት አዲስ አምባሳደር ጋር በተገናኙበት ግዜ መግለጻቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስገንዝበዋል ።

ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እኤአ በ200 ቡልጋርያን ከጐበኙ በኃላ በቅድስት መንበር እና ቡልጋርያ መካከል የነበረውን ግንኙነት በበለጠ መጠናከሩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ማስታወሳቸውም ተያይዞ ተመልክተዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.