2009-10-28 14:09:45

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሁሉም አርመናውያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ካረኪን ሁለተኛ መልእክት አስተላለፉ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና በካቶሊኪስ የሁሉም አርመናውያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ካረኪን ሁለተኛ ፓትሪያርክ ሆነው የተመረጡበት 10ኛው ዓመት ምክንያት መልእክት RealAudioMP3 ማስተላለፋቸው ተገለጠ።

ቅዱሱነታቸው ለሁሉም አርመናውያን ሊቀ ጳጳሳት እና ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ካረኪን ሁለተኛ ባስተላለፉት መልእክት፣ በሁለቱም አቢያተ ክርስትያን መካከል ለውህደት ያቀና በመከናወን ላይ ያለው ግኑኝነት ወደ ፊት መራመዱ እና እድገትም እያሳየ መሆኑ በመጥቀስ፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና በሓዋርያዊት የአርመን ቤተ ክርስትያን መካከል ያለው ግኑኝነት በበለጥ እንዲሻሻል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ካረኪን ሁለተኛ ያሳዩት ዓቢይ ጥረት በመጥቀስ ምሥጋና ማቅረባቸው ተገለጠ።

ይህች ሓዋርያዊት የአርመን ቤተ ክስርትያን ነጻነቷን በመቀዳጀት እያከናወነቸው ያለው ክርስትያናዊ ሰብአዊ ሕንጸት የሚደነቅ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በመጥቀስ፣ ለሰው ልጅ ለተሟላ እድገት መሠረት መሆኑም በመግለጥ፣ እምነት ተስፋ እና ፍቅር መርሕ በማድረግ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የአርመን ሓዋርያዊት ቤተ ክርስትያን መካከል ግኑኝነታቸውን ዘወትር ያሳይሉ ዘንድ ባቀረቡት ጸሎት መልእክቱን መደምደማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

እ.ኤ.አ. ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ ካረኪን ሁለተኛን በቫቲካን ተቀብለው ባነጋገሩትበ እለት መንፈስ ቅዱስ የተዘጉ በሮች ይከፍት ዘንድ መማጠናቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ብፁዕ ወቅዱስ ካረኪን ሁለተኛ በበኩላቸውም ር.ሊ.ጳ. የክርስትና መሠረት በሁሉም ዘንድ በሚገባ እንዲታወቅ እና በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው ግኑኝነት እንዲያይል ላከናወኑት እና እያከናወኑት ያለው ጥረት በመጥቀስ ምስጋና ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መገልጫ በማስታወስ ይጠቁማል።

የቤተክርስትያን ታሪክ መሠረት፣ በ 310 ሓዋርያት በርጠለሚዮስ እና ታደዮስ ለአርመን ህዝብ ወንጌልን መስበካቸው እና በ 301 ዓ.ም. በቅዱስ ጎርጎርዮስ ከሳተ ብርሃን ድንቅ ሓዋርያዊ አገልግሎት መሠረት ክርስትናን መቀበላቸው ሲገለጥ፣ ለዚህም ነው የአርመን ቤተ ክርስትያን ጎርጎሪዮሳዊት ቤተ ክርስትያን ተብላ የምትጠራው።

የአርመን ቤተ ክርስትያን ቀደምት ሶስቱ የቤተ ክርስትያን ጉባኤዎችን ስትቀበል በ 451 ዓ.ም. የተካሄደው የቀልቄዶኒያ ጉባኤ ሳትቀበለው በመቅረት፣ ከራስዋ ሃይማኖታዊ መሪ በስቀረ ማንም የለም በማለት የምታምን ቤተ ክርስትያን ሆና መቅረቷ ሲታወቅ። እ.ኤ.አ. በ 1996 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ካረኪን አንደኛ በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን መካከል ያለውን ልዩነት ለማስወገድ የሚረዳ የጋራ የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.