2009-10-19 16:14:11

የአፍሪቃ ጳጳሳት ኢትዮጵያዊ ኮለጅ ጉብኝት ፡


በዚሁ በተያዝነው ጥቅምት ወር እዚህ ቫቲካ ውስጥ የተጀመረው የአፍሪቃ አህጉር ካቶሊካውያን ጳጳሳት ሁለተኛ እና ልዩ ሲኖዶስ እየቀጠለ ነው ።

ብፁዓን ጳጳሳት አፍሪቃ ትናንትና ሰንበት ዕረፍት አድርገው ዛሬ ፡ በተናንሽ የወይይት ጥናት እና ምክክር ቡድኖች ተከፋፍለው አርፍደዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የሰካም በየአፍሪቃ እና ማዳካስካር ረኪበ ጳጳሳት በታንዛንያ የደሬሰለም ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ ካርዲናል ፐንጎ የተመሩ አራት አፍሪቃውያን ጳጳሳት በየሮማ ማዛግጃቤት ተገኝተው የአፍሪቃ እና ሮማ ከተማ አጋርነት በተሰየመ ርእስ ዙርያ ለማዛጋጃ ቤቱ ባለስልጥናት እና የጣልያን መገናኛ ብዙኀን ሰፊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የሮማ ከተማ ከንቲባ ጂያኒ አለማኖ ሮማ ከተማ እና ኢጣልያ ከአፍሪቃ ሀገራት ጋር በእድገት በኩል ለመተባበር ያላቸውን ፕሮግራሞች እና ከሀገራቱ ጋር ያለውን ግኝኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በቅድስት መንበር የጳጳሳት ጉብኤ ዋና ጽሐፊ ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች የቅድስት መንበር ቃል አቃባይ እና ተሬድዮ ቫቲካን ስራ አስኪያጅ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ መስራች ፕሮፈሶር አንድረአ ሪካርዲ በዚሁ ግኙኝነት ተገኝተው ንግግር አሰምተዋል።

ይሁን እና ጳጳሳቱ ዛሬ አምሻቸው እዚህ ሮማ ውስጥ በሚገኘው አውዲቶርዩም የአፍሪቃ ኪነ ጠበብት ያዘጋጅቱን አፍሪቃው ትዕይንተ ሙዚቃ ይታዘባሉ ፡

ከትናንትና ወድያ የአፍሪቃ እና ማዳካስካር ረኪበ ጳጳሳት አህጉራዊ ጉባኤ ሊቀመናብርት በአጠቃላይ ከአርባ የሚበልጡ አፍሪቃውያን ጳጳሳት በቫቲካን አትክልት የተከበበው እና ቫቲካን ውስጥ የሚገኘው ጥንታዊ እና ታሪካዊ ኮሌጅ ገብኝተው ነበር እና የዛሬ ዝግጅታችን በዚሁ ያተኮረ ይሆናል ።

ከዚህ ቀጥሎ ሊቀ ጳጳሳት ዘ ካቶሊካውያን ኢትዮጵያ ብፁዕ አቡነ ብርሃነ የሱስ ሱራፊኤል የአፍሪቃውያን ጳጳሳት ኢትዮጵያዊ ኮሌጅ ጉብኝት እና ያደረባቸው ስሜት ትኩረት ሰጠው ለአማጮጫችን ማብራርያ ሲሰጡ ታዳምጣላችሁ። RealAudioMP3



 








All the contents on this site are copyrighted ©.