2009-10-16 13:47:59

የካቶሊክ እና የፕሮተስታንት ቤተ ክርስትያን የጋራ ውይይት


የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ከሌሎች አቢያተ ክርስትያናት ጋር የምታካሄደው ግኑኝነት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር የካቶሊክ እና የፕሮተስታትን ቤተ ክርስትያን ላንድነት የሚደረገው ጥረት በአንዲስ መንፈስ የሚያነቃቃ እና ውይይት ወደ ፊት እንዲል የሚያግዝ አዲስ መጽሓፍ RealAudioMP3 መድረሳቸው ተገለጠ።

ይህ ፍሬውን ለመስብሰብ በሚል ርእስ ሥር ሎንደን በሚገኘው ኮንቲኒውም ማተሚያ ቤት አማካኝነት ለህትመት የበቃው አዲሱ መጽሓፍ፣ በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን እስካሁን ድረስ የተካሄዱት ይፋዊ የጋራ ውይይቶች ያስገኙት የክርስትናው እምነት መሠረታዊ ገጽታውን የሚያጎላው ነጥብ የሚተነትን እና የሚያስረዳ ሲሆን፣ መጽሓፉ ትላንትና እዚህ ቫቲካን በሚገኘው የህትመት እና የማስታወቂያ አዳራሽ፣ መጽሓፉን በማጠናቀር ረገድ ዋናውን ሚና በተጫወቱት በብጹዕ ካርዲናል ካስፐር እና በብፁዕ አቡነ ማርክ ላንጋም አማካኝነት መግለጫ ተሰጥቶበት ለንባብ መቅረቡ የቅድስት መንበር መገልጫ ያመለክታል።

ለሁለት ዓመተ ጥናት ሲካሄድበት ቆይቶ፣ ለንባብ የበቃው መጽሓፍ በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን መካከል አንድነት እልሞ የተካሄዱት ውይይቶች ያስገኘው አወንታዊ ውጤት በማሰባሰብ አወነታዊ ገጽታውን ለይቶ የሚያስረዳ መጽሓፍ መሆኑ፣ ብፁዕ ካርዲናል ካስፐር በሰጡት መግለጫ ጠቅሰው፣ የነዚህ አቢያተ ክርስትያን ወጣት ትውልድ የሚያሳየው መቀራረብ ጭምር የሚያጎላ ሲሆን፣ የተደረገው ውይይት ያስገኘው አመርቂ ውጤት መሠረት በማድረግ ከዚህ ቀጥሎ ለሚደረገው ውይይት የሚያነቃቃ ብቻ ሳይሆን፣ አዲስ መልክ እንዲኖረው የሚያግዝ ነው ካሉ በኋላ፣ በምዕራቡ ዓለም የሚደረገው የአቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት ምን እንደሚመስል ጭምር ያስተነተነ መጽሓፍ ነው ብለዋል።

ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወዲህ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የአቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት መሠረት የታለመው አንድነት እግብ ለማድረስ፣ ከካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጋር ውይይት የሚያካሂዱት አቢያተ ክርስትያን ስነ ምግባር በተመለከተው ረገድ ያላቸው የሐሳብ ልዩነት መሠረት፣ ጉዞው ረዥም መሆኑ ከተካሄዱት የጋራ ግኑኝነት ለመረዳት መቻሉንም ብፁዕነታቸው መጽሐፉን ለንባብ በቀረበበት እለት በሰጡት መገልጫ በማስታወቅ፣ ሆኖም ግን ይላሉ የጋራው ውይይት ጎታታ ነው ብሎ ለመፍረድ አይቻልም ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ካስፐር አክለውም ይህ መጽሐፍ በቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እና የካቶሊክ አንቀጸ ሃይምናኖት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር በኩል በሚገባ የተጤነ እና የተመረመረ መሆኑም ገልጠው፣ በዚህ አጋጣሚም ቅዱስ አባታችን ሮማ የሚገኘውን በሉተራን ቤተ ክርስትያን ሓዋርያዊ ጉብኝት ለማካሄድ እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ብፁዕ አቡነ ማርክ ላንጋም በሰጡት መግለጫ፣ መጽሓፉ አራት ምዕራፍ እንዳለው ሲያብራሩ አንደኛው ምዕራፍ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው እምነት መሠረት በሚል ርእስ የተጠናቀረ መሆኑ እና ሁለተኛው ምዕራፍ ድህነት፣ ጽደቅ እና ቅድስና የሚሉት አበይት ቲዮሎጋውያን ጥያቄዎች እነርሱም የሉተራን ቤተ ክርስትያን የእምነት ማእክል የሆኑትን ነጥቦች መሠረተ በማድረግ የተካሄደው የጋራው ውይይት የሚተነትን፣ ሶስትሰኛው ምዕራፍ ደግሞ ስነ ቤተክርስትያን የሚመለከት ሲሆን፣ አራተኛው ምዕራፍ ሚስጢረ ጥምቀት እና ቅዱስ ቁርባን በሚል ርእስ ሥር የተጠናቀረ መሆኑ ገልጠው፣ በማጠቃለያው ርእስ ሥር ብጹዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር በ 16ኛው ክፍለ ዘመን ተነስተው የነበሩት በአሁኑ ወቅት መፍትሔ ያገኙት አከራካሪ የእምነት ጥያቄዎች፣ ታሪካዊ አመጣጥ እና የሚያስተጋቡት ቲዮሊጊያዊ ስነ ሀሳብ የሚያብራራ መሆኑ በሰጡት መገለጫ አብራርተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.