2009-10-12 13:41:47

የአፍሪቃ ሲኖዶስ ጉባኤ ባለፈው ሳምንት የዳሰሳቸው ጉዳዮች


እዚህ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብጹዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ባለፈው ቅዳሜ የላቲን ሥርዓት የምትከተል ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የአፍሪቃ ሰባኪ ወንጌል እና የአፍሪቃ ጠባቂ ቅዱስ ዳኒኤል ኮምቦኒ RealAudioMP3 ባከበረችበት እለት የአንደኛ ሳምንት ጉባኤውን ማጠቃለሉ ሲገለጥ ይህ አጋጣሚም የእግዚአብሔር አሳቢነት ለአፍሪቃ ያጎላ መሆኑ ለመረዳትም አያዳግትም።

የአፍሪቃ ሲኖዶስ አበው የቅዳሜው ጠዋት ስብሰባቸውን አጠናቀው በሮማው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ልክ 06 ሰዓት ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድተኛ የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስ አባታችን ሮማ ከሚገኙት መናብረተ ጥበብ ተማሪዎች ጋር በመሆን ለአፍርቃ ከአፍሪቃ ጋር በሚል መንፈሳዊ መርህ በመሩት የመቁጠሪያ ጸሎት መሳተፋቸው ሲገለጥ። ይህ የመቁጸሪያው ጸሎት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን በኩል በቀጥታ በግብጽ ኬኒያ ሱዳን ማዳጋስካር ደቡብ አፍሪቃ ናይጀሪያ ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ ሞዛምቢ እና በሙርኪና ፋሶ መሰራጨቱ ተገልጠዋል።

በዚህ በተካሄደው የመቁጸሪያ ጸሎት ቅዱስ አብታችን ባሰሙት ንግግር የአፍሪቃ አዲሱ ስብከተ ወንጌል በአፍሪቃ ተማሪዎች ትጋት የሚከናወን መሆኑ በማሳሰብ፣ የዚህች ክፍለ ዓለም ወጣቶች በጸሎቴ ህያው ናቸው ካሉ በኋላ፣ ወጣቱ የህብረተሰቡ ክፍል ተገቢ እና የተሟላ ሕንጸት በማግኘት ለአፍሪቃ የተሟላ እድገት ዋና ተዋናያን ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ትምህርት እውነት የሚፈለግበት የተሟላ ሰብአዊ እድገት የሚረጋገጥበት መሆን እንዳለበትም በመግለጥ፣ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ በር የሚክፍት መሆን አለበት፣ የስነ ፍጥረት እውቀት ባህል በሚያሰራጩ የተለያዩ በተለይ ደግሞ በአፍሪቃ መናብረተ ጥበብ መካከል ግኑኝነት እና ትብብር ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመጨረሻውም በተለያዩ የኤውሮጳ መናብረተ ጥበብ የሚገኙ የአፍሪቃ ተማሪዎች ለአፍሪቃ የነገ ብሩህ ተስፋ መሆናቸው መቼም ቢሆን ሳይዘነጉ፣ በአገሮቻቸው ሰብአዊነት የተካነው ባህል የሚያነቃቁ አዲስ ኃይል መሆናቸውም አውቀው፣ የሚያካሂዱት ባህላዊ ቅድመ ዝግጅት በኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸው እንዳሉም ተገልጠዋል።

በተካሄደው የመቁጸርያ ጸሎት አማካኝነት ስለ አፍሪቃ ሴቶች እና ስደተኞች ጉዳይ አስተንትኖ መደረጉ ለማወቅ ሲቻል፣ ለአፍሪቃ ሰላም እርቅ እና ፍትህ ማእከል የቦታው ቤተ ክርስትያን ማለትም ከቤተሰብ የሚጀመር መሆኑ እግምት ውስጥ ያስገባ የጸሎት ሥርዓት እንደነበር ከሥፍራው የተላለፈው መገልጫ ይጠቁማል።

በዚህ በተካሄደው የመቁጸሪያ ጸሎት በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች የሚኖሩ ስደተኞች ተሳትፈዋል። ብፁዓን ጳጳሳት ስደተኞች ዜጎቻቸውን አቀርበው ለመመልከት ያስቻላቸው አጋጣሚም እንደነበርም ለማወቅ ተችለዋል።

ብፁዓን ጳጳሳቱ ባካሄዱት የሳምት ጉባኤ በአፍሪቃ በመስፋፋት ላይ ያለው የሻራ ሃይምኖት ሂደት ለመግታት የሚያግዝ ግብረ ኖልዎ ማረጋገጥ፣ አነስተኛ ብድር ማለትም የቁጠባው ኤክኖሚ ማነቃቃት ወሳኝ መሆኑ እንዳመለከቱ እና ስለ ስደተኛው ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲሁም ስደተኛው ዜጋ የሚያጋጠምው እና የሚኖረው ቅይጥ ጋብቻ በመዳሰስ ባህላቸውን አቅበው ከሚኖርበት አገር እና ህዝብ ጋር ተዋህደው በሁሉም ማህበራዊ ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ ዜጋ ለመሆን እንዲተጉ ብፁዓን ጳጳሳቱ አስገንዝበው፣ የስደተኛው ጸዓት ለመግታት የሚደረገው ጥረት ጸረ ስደተኛ ህግ በማረማመድ ሳይሆን የአፍሪቃ ድኽነት ለመቅረፍ በሚያግዝ ሥልት መሆን እንደሚገባው የሲኖዶስ ብፁዓን አበው በማሳሰብ፣ አፍሪቃ ያለባት የውጭ አገር የብድር ጫና ይሰርዘም ዘንድ ጥሪ በማቅረብ፣ በአፍሪቃ የሚታዩት ግጭቶች ቀርቦ የሚመለከት እና መፍትሔ የሚያፈላልግ አንድ ቋሚ ያለም አቀፍ ታዛቢ ድርገት ይመለመልም ዘንድ ማሳሰባቸው ተገልጠዋል።

የተባበሩት መንግሥታትን ወክለውም ለሲንዶስ ንግግር ያሰሙት በዳርፉር ለተባበሩት መንግሥታት እና ለአፍሪቃ ኅብረት የጋራ ድርገት ሊቀ መንበር ሩዶልፍ አዳዳ፣ ግጭቶች በወታደራዊ ኃይል ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ለብቻው ብቃት የሌለው ጎዶሎ መሆኑ በማሳሰብ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ስምምነት ማረጋገጥም እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ማብራራታቸው እና ቤተ ክርስትያን የሰላም ኃይል ነች በማለት በአፍሪቃ በጠቅላላ በዓለማችን ሰላም ለማረጋገጥ የቤተ ክርስትያን ተሳታፊነት ወሳኝ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.