2009-10-05 14:21:38

ጥቅምት ወር የር.ሊ.ጳ. ስለ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ጸሎት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. በነዲክቶስ 16ኛ የካቶሊክ ባህል መሠረት በያመቱ ጥቅምት ወር ስለ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ የሚጸለይበት ወር መሆኑ በመጥቀስ በዚህ 2009 ዓ.ም. ጥቅምት ወር፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሐዋርያዊው ግብረ ተልእኮ፣ RealAudioMP3 ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ስበኩ በሚል ክርስቶስ በሰጠው ሐዋርያዊ የግብረ ተልእኮ ኃላፊነት ተመርቶ እግብር ላይ እንዲያውል በማሳሰብ፣ ይኽ የተሰጠው የግብረ ተልእኮ ኃላፊነት ከፍተኛ እና የላቀ ለሰው ልጅ የሚሰጥ ክቡር አገልግሎት ነው ብለዋል።

ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ ሲል በአንደኛይቱ ለቆሮንጦስ ክርስትያን በጻፋት መልእክት እራሱን በማስጠንቀቅ በዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ቅናት ተገፋፍቶ የክርስቶስ መልእክት ለሁሉም ለማዳረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ጥሪ ምላሽ እንደሰጠ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ገልጠው፣ ቀደምት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን አርእስተ ሊቃ ጳጳሳትን በተለይ ደግሞ የር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ ቀድሞ የማጤን የላቀው ብቃት እርሱም የዛሬ 83 ዓመት እ.ኤ.አ. በ 1962 ዓ.ም. ረሩም ኤክለሲያ - የቤተ ክርስትያን ወንጌላዊነት የሚያሳስብ ወንጌልን ለሁሉም ለማድረስ መጠራቷ እና ይኸንን ሐዋርያነት ባህርይዋ የሚያሳስብ በጻፉዋት አዋዲት መልእክት አማካኝነት ጥቅምት ስለ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ እንዲጸለይ የሰጡት ውሳኔ በመዘከር፣ ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. ፍቅር የሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ማእከል መሆኑ በማብራራት፣ በፍቅር ያልተመራ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ኅብረተሰብን ከማሰብ የሚፈጸም ሰብአዊ አገልግሎ ብቻ ሆኖ እንደሚቀር ገልጠው፣ እያንዳንዱ ክርስትያን ከሚሥጢረ ጥምቀት የተቀበለው ጸጋ በመኖር፣ በክርስቶስ ተልእኮ ተሳታፊ በመሆኑ ዓለምን ለማዳን የፈለገው የእግዚአብሔር አዲስ ኪዳን እርሱም እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑ ማብሰር እንደሚገባው እና እያንዳንዱ ልኡክ በሁሉም ዘርፍ በርትቶ ወንጌልን በማካፈል እና በደስታ እንደሚኖረውም መመስከር ይኖርበታል እንዳሉ የሚዘከር ነው።

ቀጥሎም በ 2007 ዓ.ም. ሁሉም አቢያተ ክርስትያን የሐዋርያዊው ግብረ ተልእኮ ኃላፊነት እንዳላቸው ጠቅሰው፣ ይህ ደግሞ ስደት መከራ እና መሥዋዕትነት የሚጠይቅ ከክርስቶስ የተሰጠ ኃላፊነት መሆኑ ገልጠው፣ እንደ ነበርም ይታወሳል። እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. ተቀዳሚው የሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ አገልግሎት ጸሎት ነው በማለት፣ ወንጌልን ለመስክበ እና ላልደረሰው ሕዝብ የማቅረብ ቅዱስ ዓላማ በጸሎት መመራት እና መጀመር እንዳልበት አሳሰበው እንደ ነበርም ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.