2009-10-02 14:38:50

መለወጥ የፍትሕ እና የእርቅ ጎዳና ነው


ሓቅን ለማወቅ መልካም የሆነውን ነገር ለመምረጥ ፍትሕ እርቅ እና ፍቅርን መከተል የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑ የናይጀሪያ ብፁዓን ጳጳሳት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 7 ቀን እስከ ከጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ባካሄደው ይፋዊ ጉባኤ RealAudioMP3 ፍጻሜ ባወጣው መግለጫ ያመለክታል።

መለወጥ ፍትሕ እና እርቅ ለማረጋገጥ የሚሸኝ መንገድ መሆኑ የገለጡት የናይጀሪያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባወጣው የጋራ መገልጫ የሰው ልጅ ልብ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንድሆንና ይኽ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ አርአያ እና አምሳያ ሆነ መፈጥሩ ዳግም በማረጋገጥ በእለታዊ ኑሮው ይመሰክረውም ዘንድ ማሳሰቡ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

በዚህች አገር እጅግ እየተስፋፋ ያለው ሙስና ሥርዓተ አልቦነት የወጣቱ የመጪው እድል እያጨለመ እና ይህ የኅብረተሰብ ክፍል የሆነው የአገር ተረካቢው ትልውድ ያለው ተስፋ እየጨለመ ለተለያዩ አደጋዎች እንዲጋለጥ እያደረገ መሆኑ በማሳወቅ፣ የዚህች አገር የተፈጥሮ ሃብት ለአገር እና ሕዝብ ጥቅም እንዳይውል የሚፈጸመው ኢፍትሃዊነት ሁከት የሚቀሰቅስ በመሆኑም ምክንያት፣ ሰላም እንዲጎድል እያደረገ ነው እንዳሉም የዜናው አገልግሎት አስታወቀ።

በመጨረሻም መንግሥት የደልታው ችግር ለመፍታት የክልሉ የልማት እድገት ለማረጋገጥ የወጠነው እቅድ ብፁዓን ጳጳሳት በመደገፍ ይህ ውሳኔ እግብር ላይ ይውል ዘንድ አደራ ብለው፣ በተጨማሪም ሃይማኖት ተገን ያደረገ እየተስፋፋ ያለው ግጭት አለ መግባባት ጸረ ሃይማኖት መሆኑ በማብራራት ሃይማኖት የሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ሊሆን አይችልም፣ እግዚአብሔር በስሜ አድኑ እንጂ ሕይወትን አጥፉ አላለም በማለት የሕይወት ባህል እንዲስፋፋ ማሳሰባቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.