2009-09-30 13:47:13

የጎዳና ተዳዳሪዎች ግብረ ኖልዎ


የጎዳና ተዳዳሪዎች ግብረ ኖልዎ አንደኛው ኤውሮጳዊ አቀፍ ጉባኤው እዚህ በቫቲካን በሚገኘው የስደተኞችና የመንገደኞች ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሕንጻ ባለው የቅዱስ ካሊስቶ የጉባኤ አዳራሽ ከ 17 የኤውሮጳ RealAudioMP3 ጳጳሳዊ ምክር ቤት የጎዳና ተዳዳሪዎች ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ድርገት ተጠሪዎች በማሳተፍ መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ ይህ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ስብሰባ የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 15 እርሱም “እየተነጋገሩ እና እየተወያዩ ሳሉም ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ጀመረ…” የሚለውን ወንጌላዊ ቃል መርህ በማድረግ እንደተካሄደም የስደተኞች እና መንገደኞች ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ ለቫቲካን ረዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች መንፈሳዊ ሰብአዊ ብሎም ቁሳዊ ድጋፍ ለማቅርበ ቤተ ክርስትያን ኃላፊነት እንዳላት በማስታወስ፣ በተለይ እነዚህ በተለያዩ ሰብአዊ ኤኮኖሚያዊ ማኅበራዊ ችግር ተገፋፍተው ተነጥለው አለ ቋሚ መጠለያ የሚንከራተቱ አብሮአቸው የሚጓዘውን ኢየሱስ በመመስከር ከወደቁበት ችግር ለማላቀቅ ያቀና ግብረ ኖልዎ እግብር ላይ ለማዋል አቢይ ጥረት፣ መንፈሳዊነት የሚጠይቅ ነው ሲሉ፣ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርኬቶ ክብር ሰራዥ በሆነው ተግባር ተሰማርተው በጎዳና የሚተዳደሩ ሴቶች፣ ሕፃናት ብዛት ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ መምጣቱ አስታውሰው፣ በጠቅላላ ከ 150 እስከ 250 ሺሕ ሕፃናትን የሚመለከት እና ቋሚ መጠለያ የሌላቸው ተከስቶ ባለው የሌኮኖሚ መቃወስ ምክንያት ብዛታቸው ወደ 3 ሚሊዮን እንደደረሰም በመግለጥ በጎዳና ለሚተዳደሩት ለመንገደኞች እና ለስደተኞች የሚመለከተው ግብረ ኖልው እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.