2009-09-29 15:22:39

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሮማው መንበረ ጥበባት ተማሪዎች ስለ አፍሪቃ ጽሎተ መቁጠሪያ ያደርሳሉ


እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አራት ሰዓት ቅዱስ ኣባታች ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሮማው መንበረ ጥበባት ተማሪዎች ለአፍሪቃ እና ከአፍሪቃ ጋር በጳውሎስ ስድስተኛ ሐዋርያዊ አዳራሽ የመቁጠርያ ጸሎት ይደግማሉ።

የመቁጠርያ ጸሎተ ሥርዓት በካይሮ በናይሮቢ በካርቱም በኣንታናናሪቭ በጆሃንስበርግ በኦኒትሻ በኪንሻሳ በማፑቶ እና በኡጋዱጉ በጋራ የሳታላይት ግኑኝነት በሚሰጠው አገልግሎት በኩል ይተላለፋል።

የመቁጠርያ ጸሎተ ሥርዓት እንዳበቃም የፍኖተ መስቀል ጸሎተ ሥርዓት ይከናወናል።



ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ. ጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ከአፍሪቃና ስለአፍሪቃና ጸሎተ መቍጠርያ በመሩበት ጊዜ ያቀረቡት ስብከትን በጣልያነኛ ቋንቋ እዚህ: RealAudioMP3 በመንካት ለማዳመጥ ይቻላል።








All the contents on this site are copyrighted ©.