2009-09-29 15:22:22

ለምን ልዩ ሁለተኛ የአፍሪካ ብጹዓን ጳጳጳሳት ሲኖዶስ አስፈለገ?


ቤተ ክርስትያን በአፍሪካ ማኅበረሰብ ዘንድ በሕንጸት ተቋማት እና በጤና ጥበቃ እንዲሁ በልማት መስኮች ተሰማርታ ለሁሉም ያቀና ዐቢይ እና ጥልቅ አገልግሎት እያከናወነች መሆኗ ለሁሉም ግልጽ ነው፣ ቤተ ክርስትያን ለዚህ ክፍለ ዓለም ያላት እይታ እና አቀራረብ የክልሉ ማኅበረሰብ ክርስትያን ካለው ዕለታዊው እና ተራ ኑሮ አማካኝነት በሚገልጠው ተጨባጩ የሕይወት ምንጭ ላይ የተገነባ ነው።

የዛሬ 15 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን የተካሄደው አንደኛው የአፍሪካ ብፁዓና ጳጳሳት ሲኖዶስ አሳማኝ ምስክርነት ኦርቅ ፍትሕ እና ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉት ሁኔታዎችን ለማጉላት እንዲቻል ቤተ ክርስትያን የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሚለው አርአያ ትከትል ዘንድ ሀሳብ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፣ ስለዚህ የክፍለ ዓለሙ ማኅበረ ክርስትያን ለፍትሕ ለሰላም በማነጽ የቤተ ክርስትያን ትንቢታዊ ተግባር በማሳየል ሠራተኞች በተስተካከለ በፍትሓዊ ገቢ እንዲተዳደሩ እና የሰላም እና የፍትሕ ድረገቶች እንዲቋቋሙ ታነቃቃለች።

ከዚህ እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የአፍሪካ ሲኖዶስ ወዲህ፣ ምንም’ኳ አሁንም አንዳንድ መሻሻል የሚገባቸው ለምሳሌ መሠረታዊ የሰብአዊ ጉዳይ የሚመለከቱ ችግሮች ብዙ ለውጥ ያላሳየ እና ስለዚህ ጉዳይ በተመለከተ የሚሰጡት መገልጫዎች እና አኅዛዊ ጥቆማዎች የዛሬ 15 ዓመት በፊት ተነስተው የነበሩት ሃይማኖታዊ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ነክ ጉዳዮች መልሶ ጠለቅ ባለ ሁኔታ እንዲጤኑ የሚያሳስብ ቢሆንም ቅሉ፣ የአፍሪካ ማኅበረሰብ ይዘት እና አገባብ ዐቢይ ትርጉም ባለው ሁኔታ እንዲሻሻል አድርገዋል።

ስለዚህ የአፍሪካ ቤተ ክርስትያን የመሬት ጨው እና የዓለም ብርሃን (ማቴ. 5፣ 13-14) እንደመሆኗም መጠን በአዲስ የወንጌል አድማስ ተመርታ በተወሃሃደ ተልእኮዋ አማካኝነት ኅብረሰተብን ለማገልገል መጠራቷ በማመን በዚሁ ጉዳይ ላይ ትኵረት በመስጠት ታስተነትናለች።

የአፍሪካ አብያተ ክርስትያን የሚያጋጥመው አዳዲስ እና አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በጋራ አስቸኳይ መልስ ለመስጠት የተጠሩ እንደ በመሆናቸው መጠን እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን ሁለተኛው የአፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ቤተ ክርስትያን በአፍሪካ ለዕርቅ ለፍትሕ እና ለሰላም አገልግሎት በሚል ርእስ ሥር እንዲካሄድ ተጠርተዋል።

አንዳንድ የአፍሪካ ቤተ ክርስትያን በ 1994 ዓ.ም. የተካሄደው አንደኛው ሲኖዶስ በሰጠው መመሪያ መሠረት በግብረ ኖልዎ በወንጌላዊ ግብረ ተልእኮ እና የተልያዩ ክርስትያን ማኅበርሰብ ላስተንትኖ ለጥናት የእግዚአብሔር ቃል ለመካፈል፣ ስብከተ ወንጌል ለቤተሰብ የወጣቶች ጉዳይ የሚመለከት ሓዋርያዊ አገልግሎት የግጭት ተቀናቃኞች በሰላም መድረክ ማገናኘት ድኽነትን ለመዋጋት፣ የፍትህ እና የሰላም ድርገቶች የመገናኛ ብዙኃን በማቋቋም እና በማጠናከር በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ውይይት በማነቃቃት ከአፍሪካ ባህላውያን ሃይማኖቶች፣ ከምስልምናው ሃይማኖት ጋር የሚደረገው ሁለገባዊ ውይይት ጭምር በማነቃቃት የኤይድስ በሽታ ለመዋጋት የጤና ጥበቃ እቅዶችን በማረጋገጥ የወንጌል ግብረ ተልእኮ ለመደገፍ በሚሉት ዕቅዶች አማካኝነት እግብር ላይ ሲያውሉት ታይተዋል።

ያም ሆነ ይህ ግን የአፍሪካ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የምትከላከላቸው እሴቶች ማለትም ቤተሰብ የሰው ልጅ ሕይወት ቅዱስ መሆኑ የምትገልጠው የምታስተምረው ትምህርት ለመቃወም የተለያዩ የፖለቲካ አካላት ተገን ከሚያድረጉዋቸው የተለያዩ የክርስትያን የሸራ ሃይማኖቶች የሚሰነዘርባት ጥቃት ቀላል እንዳልሆነ እና ይኽ አይነቱ አሉታዊ ገጠመኝ ብዙውን ጊዜ እንደሚያጋጥሙዋት በሕዝባዊ መድረኮች እንደሚደርስባትም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።

በአንዳንድ የክልል አብያተ ክርስትያን እና ማኅበረ ክርስትያን መካከልም ጎሳዊ ክልላዊ ብሔራዊ እንዲሁም በአንዳንድ የነፍሳት እረኞችም ሆን ብለው የሚቀሰቅሱት የዘር ልዩነት የመሳሰሉት ችግሮች ጎልተው ይታያሉ። በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ካህናቶታቸውም መካከል አለ መግባባት የሚታይ ሲሆን፣ በአንድ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዘንድ የአንድ የፖለቲካ ሰልፍ ወይንም አመለካከት የሚደግፍ ሀሳብ እና የሚያመለክት ውሳኔ ሲተላለፍም ይታያል።

ስለዚህ እነዚህ ሕዝባዊ እና ቤተ ክርስትያናዊ ገጠመኞች፣ ውህደት እና አንድነት በማነቃቃት እንዲሁም ብፁዓን ጳጳሳት እና ካህናት ትምቢታዊ ብርታት አግኝተው በእምነት የጸኑ በፖለቲካው አለም የሚያገለግሉ አለማውያን ምእመናን ለማዘጋጀት የተለያየ በማኅበረሰብ ዘንድ ያለው ልዩነት የህዝቡ በሰላም የመኖሩ ሂደት እንዳያናጋ በሰላም ለመኖር የሚያስችላቸው ወንድማማችነት እንዲሰርጽ ለማድረግ የሚያግዙ መንገዶች እንድታፈላልግ የሚያነቃቃት ጥያቄ ሆኖባት ይታያል። የዘመናችን ትእምርት የእግዚአብሔር መንግሥት ምስክሮች ለመሆን የሚያበቃ ሕንጸት ለካህናት እና ለገዳማውያን እንዲሰጥ በዚሁ ጉዳይ ልዩ ትኵረት እንዲሰጥ እና የአፍሪካ ባህል የሚያንጸባርቃቸው ሐቆች እና እሴቶች በወንጌል እንዲነኩ እና እንዲለወጡ የሚያግዝ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ጭምር ያበረታታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.