Home Archivio
2009-09-28 14:48:11
ሶማሊያ፣ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች
በሶማሊያ በጊዚያዊ መንግሥት የመከላከያ ህይል እና ተቃዋሚው እስላማዊ ግንባር መካከል በመካሂድ ላይ ባለው ግጭት ሳቢያ ለመፈናቀል ለስደት የዳረገ 50 ሺሕ የሚገመቱት ያገሪቱ ዜጎች በኬኒያ የስደተኛው መጠለያ ሰፈር
እንደሚገኙ ሚስና የዜና አገልግሎት በመጠቆም ሆኖም የመጠለያ ሰፈሮች በስደተኛ ብዛት በመጨናነቅ እያስከተለው ያለው የጤና መታወክ እና የበሽታ መዛመት ብሎም ሁከት ለመግታት ካሉት ስደተኞች ውስጥ ገሚሶቹን ወደ ሌላ መጠለያ ሰፈር ለማዘዋወር መወሰኑም የዜናው አግልግሎት በመግለጥ በክልሉ እየታየ ያለው ኃይለኛው ዝናብ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ መሻሻል እንዳሳየም እቅዱ ገቢራዊ እንደሚሆን ሚስና የክልሉ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት የሰጠው መገልጫ በመጥቀስ አስታውቀዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.