2009-09-25 14:11:02

የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍልጎቶችን ለማርካት


እ.ኤ.አ. በ 2050 ዓ.ም. የአለማችን ህዝብ ብዛት ካለበት በ 2 ሚሊያርድ እና 300 ሚሊዮን ህዝብ ከፍ እንደሚል ስለዚህ ለዚህ በ 2050 ዓ.ም. ለሚኖረው የአለም ህዝብ መሠረታዊ ሰብአውያን ፍላጎቶች ለማርካት የሚቀርበው ምርት RealAudioMP3 ካለበት በ 70% ከፍ ምድረግ ወሳኝ መሆኑ የዓለም አቀፍ የእርሻና የምግብ ድርጅት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

የድርጅቱ መግለጫ እንደሚያመለክተውም ምርትን ከፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ድኽነት ርሃብ የመሳሰሉት ብዙ ሕዝብ እያሰቃየ ያለው ችግር ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት፣ አጥጋቢ ውጤት ማስገኘት ይኖርበታል፣ ካልሆነ ግን የህዝብ ብዛት ከፍ ባለበት ቁጥር የምግብ እጥረት ችግር በዚይኑ ልክ ከፍ እንደሚል በማሳሰብ፣ ይኸንን ጉዳይ እግምት ውስጥ በማስገባት ድርጅቱ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 12 እስከ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ ሮማ በ 2050 ዓ.ም. የዓለም ሕዝብ መሠረታዊ የምግብ ፍላጎት ለማርካት በሚል ርእስ ሥር የሚመራ ዓለም አቀፍዊ ጉባኤ ጠርተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.