2009-09-25 14:08:08

ውህደት እና ምስክርነት


እ.ኤ.አ. ከ ጥቅምት 10 እሰከ ጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የመካከለኛው ምሥራቅ ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ “ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመካከለኛው ምሥራቅ ውህደት እና ምስክርነት” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ ሊካሄድ መወሰኑ RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ እንዳመለከተው የሚታወስ ነው። ስለ ጉዳዩ በማስመልከት አርመናዊ የቅልቂያ የካቶልክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኔርሰስ ቤድሮስ አስራ አንደኛ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዮርዳኖስን እና በቅድስት መሬት ሓዋርያዊ ጉብኝት በማከናወን የክልሉ ካቶልክ ቤተ ክርስትያ በመጎብኘት እና ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ባካሄዱት ሰፊ ውይይት መሠረት የክልሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መሠረታዊ ጥያቄዎችን አቢይ ግምት በመስጠት በ 2010 ዓ.ም. እንዲካሄድ የወሰኑት የመካከለኛው ምሥራቅ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በአይነቱ በቤተ ክርስትያን ታሪክ የመጀመሪያ ነው ብለዋል።

የዚህ ክልል ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ውህደት እና ምስክርነት ማእክል ያደረገች መሆን ይገባታል፣ ከውህደት የመነጨ ምስክርነት የሚያሳምን እና ማራኪ ምስክርነቱ ታማኝ እንደሚያደርግ ብፁዕ ወቅዱስ ኔርሰስ ቤድሮስ አስራ አንደኛ በመግለጥ፣ የዚህ ክልል ቤተ ክርስትያን ከምስልምናው እና ከአይሁድ ሃይማኖት ጋር ግኑኝነት እንዳላት ጠቅሰው፣ ሁሉም ሃይማኖቶች ከ 60 ዓመት በላይ የሆነው የዚህ ክልል ሰላም የማጣት ጉዳይ ሁከት እና ውጥረት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በሚድረገው ጥረት አቢይ ኃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ገልጠው፣ በሃይማኖቶች መካከል ውጥረት ካለ በዚህ ክልል ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ከንቱ ነው፣ ይህ የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ግፊት የሚያሻው የሰላም ሂደት ፖለቲካዊ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ጉዳይ የሚመለከት ነው ካሉ በኋላ፣ ይህ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የመካከለኛው ምሥራቅ የካቶልክ ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ብዙ ተስፋ ተጥሎበታል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.