2009-09-25 14:05:21

መንፈሳዊ አንድነት ለሚረጋገጥባት ኤውሮጳ


ቀደም ሲል የቅድስት መንበር መገልጫ እንዳመለከተው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 26 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ረፓብሊክ ቼክ እንደሚጎበኙ ሲታወቅ። RealAudioMP3 ቅዱስነታቸው ፕራግን ብርኖን የዚህ ሓዋርያዊ ጉብኝት ዋናው ምክንያት የሆነው ቅዱስ ቨንቸስላኦ ሰማዕትነት የተቀበለባት እና የሰማዕትነቱ 100 ዓመት የምታከብረው በስታራ ቦለስላቭ ከተማን እንደሚጎበኙም ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይህ ነገ የሚጀምሩት ሓዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት የዛሬ 90 ዓመት በፊት በብርኖ ከተማ የተወለዱት በኮሙኒዝም ሥርዓት ወቅት ብዙ ስቃይና መከራ የደረሰባቸው የኢየሱሳውን ማህበር አባል ብፁዕ ካርዲናል ቶማስ ስፒድሊክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዛሬ 20 ዓመት በፊት ስመ ጥር የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልክ የበርሊን ግንብ በወደቀበት ዓመት ብዚሕች አገር ሓዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው አስታውሰው፣ ስለዚህ እነዚህ የታሪክ ትውስቶች የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሚያከናውኑት ሓዋርያዊ ጉብኝት ሕያው የሚያደርግ ጸጋ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ ካርዲናል ስፒድሊክ ይላሉ፣ የቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሓዋርያዊ ጉብኝት መንፈሳዊ እንጂ ፖለቲካዊ ገጽታ የሌለው መሆኑ በማሳሰብ፣ የቼክ ህዝብ ከምሥራቅ ዓለም የፈለሰ ቢሆንም ከምዕራቡ ስልጣኔ እና ባህል ጋር ከተዋሃደ ይኸው 2 ሺሕ ዓመታት እንደሆነው ገልጠው፣ ስለዚህ ይህ ህዝብ ምዕራብን እና ምስራቅን የሚያገናኝ ባህል እና ሥልጣኔ ያለው መሆኑ አስታውሰው፣ የቅዱስ አብታችን ሓዋርያዊው ጉብኝት ኤውሮጳ መንፈሳዊ አንድነት እንዲረጋገጥባት በመምራት የሚያነቃቃ ዕድል ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.