2009-09-23 13:36:24

የስደተኞች እና ተፈናቃዮች መብት እና ፈቃድ ማክበር


አምነስት ኢንተርናሽናል የሰብአዊ መብት ተሟጋች የዓለም አቀፍ ማህበር፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና የተፈናቃዮች የበላይ ድርገት፣ ሕጻናት አድን ድርጅት እና የተለያዩ የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተሉ ሌሎች ዓለም አቀፍ ማኅበራት RealAudioMP3 የተሳተፉበት ስለ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ የክብ ጠረጴዛ ውይይት እዚህ ሮማ በሚገኘው በቶር ቨርጋታ መንበረ ጥበብ መካሄዱ ተገለጠ።

በዚህ ውህደት ትብብር እና የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ማእከል ያደረገው ዓለም አቀፍ የክብ ጠረጴዛ ውይይት ምስክርት የሰጡ አንዳንድ ስደተኞች ጭምር መሳተፋቸው ሲታወቅ፣ ስደተኞችን ማስተናገድ እና ስደተኛው ተከሎ የሚኖር ተጨባጭ ክስተት እንዳይሆን ከተስተናገዱበት አገር ጋር ተዋህደው እንዲኖሩ የሚያግዛቸው ሰብአዊ ልክነት የተካነ የስደተኛ የማስተዳደሪያ ደንብ ወሳኝ መሆኑ ጉባኤው አሳስበዋል።

በተለይ ደግሞ ከስደተኛው ማህበርሰብ የሚለዱት የማህበርሰብ አባላት መሆናቸው ወላጆቻቸው የተስተናገዱበት አገር ልጆች እንጂ ስደተኞች እንዳልሆኑ የክብ ጠረጴዛው ውይይት ያመለክታል። ስለዚህ ኅብረ ባህል ኅብረ ኃይማኖት የወደፊት ወይንም ተስፋ ሳይሆን ተጨባጭ ክስተት ነው፣ ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባት ብሔራዊው ኅብረ-ኅብረተሰብ የሚያረጋገጥ የፖሊቲካ ሥርዓት አስፈላጊ መሆኑ ጉባኤው አስምሮበታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.