2009-09-23 13:34:13

ቤተ ክርስትያን ሐቅ ከማብሠር አትቆጠብም


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ከትላትና በስትያ ይፋዊ ጉባኤው በምክር ቤቱ ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ባሰሙት ንግግ በይፋ መጀመሩ ተገለጠ። ብፁዕነታቸው ባሰሙት የጉባኤው የመክፈቻ ንግግር፣ RealAudioMP3 ኤኮኖሚ፣ ፖለቲካ በስነ ምግባር የተካነ እና እንዲሁም የካቶሊክ ሃይማኖት ትምህርት አስፈላጊነቱ አሳስበዋል። ይህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካሪታስ ኢን ቨሪታተ ፍቅር በሓቅ በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት ዓዋዲት መልእክት ማእከል ያደረገው ይፋዊ ጉባኤ፣ ነገ እንደሚጠናቀቅ ከወዲሁ ሲገለጥ፣ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፣ በአሁኑ ወቅት የኢጣሊያ የሠለጠነው እና መልካሙን የአብሮ የመኖሩ ሂደት የሚያውኩ ተግባሮች በተለያየ መልኩ በመታየት ላይ መሆኑ ጠቅሰው፣ ቤተ ክርስትያን ትላትናም ዛሬም ነገም ለብዙዎች የማይስማማ ደስ የማያሰኝ ቢሆ ቢገኝም ቅሉ እውነትን ከማበሠረት ወደ ኋላ እንደማትል በመግለጥ፣ ቤተ ርክስትያን ከመሥራችዋ ልመሳሰል የማይል ይሉኝታን የማያውቅ የማያጎበድድ የወንጌል ሓቅ እንድታበሥር ተጠርታለች ብለዋል።

በዚሁ አጋጣሚም ባለፈው ሓሙስ በአፍጋኒስታን ባሸባሪዎች ሴራ ለሞት የተዳረጉት እና ከትላትና በስትያ እዚህ ሮማ ፎሮ ለ ሙራ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ የቀብር ሥነ ስርአት የተፈጸመላቸው ስድስት የኢጣልያ የሰላም ልኡካን ኣባላት በመዘከር፣ እግዚአብሔር ቤተሰቦቻቸውን እንዲጠብቅ እና እንዲያጽናናቸውም ተማጥነው፣ የከፈሉት መስዋዕትነት የሰላም ዘር ነው ብለው፣ አክለውም በቅርቡ በብራዚል አማዞን ግዛት በምትገኘው በማናውስ ከተማ የተገደሉት የወንጌል ልኡክ ኢጣሊያዊ ኣባ ሩጀሮ ሩቮለቶን በማሰብ ሓቅ ለማበሠረት የታጠቀው ግብረ ተልእኮ ቀላል እንዳልሆነ ገልጠው፣ በዚህ ዓለማ የተሰማሩት የቤተ ክርስትያን ልጆች እውነትን በማብሰር የሰው ልጅ ከተለያዩ ወጥመዶች ነጻ ለማውጣት ተጠርተዋል ብለልዋል። ፍቅር በሓቅ ዓዋዲት መልእክት በመጥቀስ፣ እውነተኛው እድገት ይላሉ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ለሕይወት ክፍት የሆነ እና የሕይወት ባህል የሚያከብር የልማት እቅድ መሆኑ ገልጠው የፖለቲካው ሥርዓት በሚስጢረ ተክሊል የጸና ቤተሰብ የኅብረተሰብ ማእከልነቱ እና ሙሉእነቱን የሚያነቃቃ መሆን ይግበዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.