2009-09-21 16:44:18

የአባ ሎምባርዲ ርእሰ ዓንቀጽ.


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የአከባቢ ሁኔታ በቅርብ እንደሚከታተሉ የሚታወስ ሲሆን ፡ባለፈው ቅርብ ግዜ በጻፋት ሐዋርያዊ መልእክትም የአከባቢ ጉዳይ ጠቅሰው ሰው ሁሉ በመርህ ደረጃ ፍትጥረት የመጠበቅ ሐላፊነት እንዳለው ማስገንዘባቸው የሚታወስ ነው።

የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ፡ በሳምንት አንድ ግዜ በየቫቲካን ተለቪስዮን ማእከል በሚያወጡት ርእሰ ዓንቀጽ እንዳመለከቱት ፡ አንዳንድ ሰዎች ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን አረጓንዴ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብለው ሲጠሩዋቸው እንደሚደመጡ ገልጠው፡

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ግዜ የአከባቢ ሁኔታ አስመልክተው በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ እና የአከባቢ ጥበቃ እንዲደረግ ሲማጠኑ መደመጣቸው አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት ሰው ሁሉ የዓላማችን ሚዛን ተሰባሪ መሆኑ እየተገነዘበ በመሄድ ላይ መሆኑ ያወሱት የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ኒውዮርክ ላይ አከባቢ ትኩረት ሰጥቶ የሚወያይ አገሮች አቀፍ ስብሰባ መጥራቱ እና ፊታችን ታሕሳስ ወር ላይ በደንማርክ ኮፐንሀገን ላይ የዓለም የሀገራት መሪዎች በዚሁ ለመሰብሰብ እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከዘላቂ እና ሰላማዊ ሕይወት የሚስማማ አዲስ ሞራላዊ የሕይወት ሥርዓተ ሕይወተ እንዲደረግ እንደሚያሳስቡ ቃል አቀባዩ በርእሰ ዓንቀጹ ላይ አስፍረውታል።

ፈጣሬ ኩሉ እግዚአብሔር ለፈጠረው፡ የሰጠው እና ያደርገለትን በጎ ተግባር ማስታወስ እንደሚገባም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስን ጠቅሰው ቃል አቀባዩ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.