2009-09-21 13:22:52

በማደግ ላይ ያሉት አገሮች ለመደገፍ


ዓለም አቀፍ የገንዘብ ሃብት ድርጅት በማደግ ላይ ያሉትን አገሮች ለመደገፍ ካለው ጠቅላላ ሃብት አንድ ስምንተኛው ቅሙጥ ሃብቱን የሚሸፍነውን 403 ቶን የወርቅ ሃብቱ ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ተገለጠዋል። RealAudioMP3

የዚህ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ሃብት ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ዶሚኒክ ስትራውስ ክሃን ይላሉ፣ ድርጅቱ የደረሰው ስምምነት በማደግ ላይ የሚገኙት አግሮች እና ድኾች አገሮች በጠቅላላ በመሠረታዊ አስፈላጊ ጉዳዮች በተመለከተ ለመርዳት እንደሚያስችለው በመግለጥ፣ በስምምነቱ እጅግ እንደረኵም አስታውቀዋል። በአለም አቀፍ ደረጃ የታየው የኤኮኖሚ መቃወስ መሻሻል እያሳየ ቢሆንም ቅሉ በድኾች አገሮች ላይ እያስከተለው ያለው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ገና ባለበት የጸና ነው ብለአዋል።

በኢንዳስትሪ በበለጸጉት 20 አገሮች በጠቅላላ እ.ኤ.አ. በዚህ በያዝነው ዓመት ብቻ የሥራ አጡ ብዛት ከ 219 እስከ 241 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል የሥራ እና ሠራተኛ ጉዳይ የሚከታተለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ዅዋን ሳሞቫይ በስትራስበርግ ከኤውሮጳ ህብረት መሪዎች ጋር ባካሄዱት ስብሰባ አስታውቀዋል።

የተከስተው አለም አቀፋዊው የኤኮኖሚ ቀውስ ለማስወገድ የበለጸጉት አገሮች የወሰዱት ውሳኔ እግብር ላይ ካልዋለ የሥራ አጡ ችግር ካለብት እንደሚብስ ሳሞቫይ በመግለጥ፣ በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች የሥራ እድል ለመፍጠር ያቀና የኤኮኖሚ እቅድ መደገፍ እና እንዲሁም የማበራዊ ደገፍ ኤኮኖሚ ማሻሻል ብሎም ማረጋገጥ ይኖርባቸውል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.