2009-09-21 16:41:04

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በረፓብሊክ ቸክ የሶስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያካሄሉ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቸክ ረፓብሊክ ቆይታቸው ርእሰ ከተማ ፕራግ ስታራ/ቦልሳቭ እና ብርኖ የተባሉ የሀገሪቱ መካኖች እንደሚጐበኙ ታውቆዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቸክ ረፓብሊክ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለመላ ሀገሪቱ ህዝብ ዓቢይ ፀጋ መሆኑ የፕራግ ከተማ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ሚሎሳቭ መግለጣቸው ተመልክተዋል ።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቸክ ረፓብሊክ ሐዋርያዊ ጉብኝት የሀገሪቱ ህዝበ እግዚአብሔር እምነት የሚያጠና እና ደስታ ሰጭ መሆኑንም ብፅዕነታቸው አያይዘው ማመልከታቸው ተነግረዋል።

የርእሰ ከተማ ፕራግ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ ካርዲናል ሚሎስላቭ ተለ ሉክስ ለተባለ የስሎቪያ ካቶሊካዊ ተለቪስዮን የሀገሪቱ ሁኔታ በተመለከተ እንደገለጹለት ፡ ኮሚኒስም ከወደቀ በኃላ ሐዋርያዊ ሙያ ለማቃናት ዓቢይ ነጻነት ገሀድ መሆኑ ጠቅስው፡ ቢሆንም የቸክ ረፓብሊክ መንግስት የቤተክርስትያን ንብረት እስካሁን ድረስ ልቤተክርትያን አልተመሰለም።

የቸክ ረፓብሊክ ቤተክርስትያን የመንግስት ጥገኛ ለመሆን እንዳማትሻ የገለጹት የፕራግ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚሎስላቭ ፡የቤተክርስትያን ንብረት በተመለከተ ከመንግስት ጋር የሚደረገው ድርድር ቀጣይ መሆኑ አያይዘው ማስረዳታቸው ተነግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ቸክ ረፓብሊክ በኮሚኒስቶች ቁጥጥር ሥር በነበረችበት ግዜ በቤተክርስትያን እና ምእመናንዋ ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ፍጹም እንደተወገደም ሊቀ ጳጳሱ መግለጻቸው የተለ ሉክስ ተለቪስዮን አገልግሎት ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.