2009-09-17 09:33:08

ዓለም ዓቅፍ የዴሞክራሲ ሥርዓት ቀን


የዴሞክራሲው ሥርዓት ለገዛ ራሱ ሊጨበጥ የሚገባው ግብ ብቻ ሳይሆን የኤኮኖሚ የማኅበራዊ እድገት የሰላም እና ያለም አቀፍ ደኅንነት ማረጋገጫ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ የመሠረታዊ ነጻነት ዋስትና ጭምር መሆኑ RealAudioMP3 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት አስምረውበታል።

የሕዝብ ተሳትፎ የሚንጸባረቅበት መንግሥታዊ አሰራር አማካኝነት የሕዝቦች እድገት እንዲረጋገጥ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አቢይ ጥረት እንደሚያደርግ የገለጠው የዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን መልእክት፣ በሕዝቦች መካከል መከባበር የመብት እና የፈቃድ እኵልነት የተረጋገጠበት ህጋዊነት የለበሰ ሥርዓት በሁሉም አገሮች እውን እንዲሆን ያሳስባል።

የዴሞክራሲው ሥርዓታ እንዳይረጋገጥ የሚያደርጉ እክሎች እንዳሉም ዘክረው ስለዚህ የሕዝብ እውነተኛው ተሳትፎ የተረጋገጠበት ሥርዓት እውን እንዲሆን የሁሉም አብይ ጥረት እና ፍላጎት ይጠይቃል፣ ስለዚህ ጉዳዩ አቢይ ኃላፊነት ነው ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ሕዝባዊ ጉዳዮች እንዲጠናከሩ እና የመዋቅሮች እድገት እንዲረጋገጥ በሁሉም ዓለም አቀፍ የውስጥ ድርጅቶቹ አማካኝነት ደገፉን እና ትብብሩን እንደሚሰጥ ብሎም ስለ ዴሞክራሲው ሥርዓት አስፈላጊ ሕንጸት እንደሚያቀርብ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.