2009-09-14 15:52:30

የሩሲያ ኦርቶዶክሳዊው ባህል


የሩሲያ ሕዝብ 70% የኦርቶዶክስ ባህል የሚያንጸባርቅ እና በኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን ትምህርት የሚያምን እንዲሁም በሁሉም ያገሪቱ ትምህርት ቤቶች የኦርቶዶስክ ትምህርተ ይሰጥ ዘንድ እንደሚሻ በ46 የሩሲያ ከልሎች የተካሄደው RealAudioMP3 የአኃዝ አጠናቃሪ ማእከል ያመልከታል። በሩሲያ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት በሚከተሉት የትምህርት እና የህንጸት መርሃ ግብር የኦርቶዶስክ እምነት ትምህርት ሊታከል መሆኑ የፈደራላዊት ሩሲያ የትምህርት ጉዳይ ሚኒ. በማሳወቅ ለመንፈሳዊ እና ለግብረ ገባዊ ሕንጸት ዓላማ መሆኑም አብራርተዋል ሲል ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

በተጨማሪም ተማሪዎች ስለ የኦርቶዶክስ የእስላም የአይሁድ እና የቡድሃ ሃይማኖት ትምህርት ለመከታተል የመምረጡ ነጻነት የሚጠብቅላቸው አንዲስ የትምህርት መርሃ ግብር መሆኑም ሚኒስትሩ ማሳወቃቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል። ይህ የፈደራላዊት ሩሲያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገቢሪያዊ እንዲሆን ጥርረት ያደረገበት አዲሱ የትምህርት መርሃ ግብር እ.ኤ.አ ከ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ገቢራዊ እንደሚሆንም ለማወቅ ተችለዋል። ይህ አዲሱ የትምህርት መርሃ ግብር 19% ብቻ እንደማይደግፈው የሩሲያው የስታቲስቲክስ የጥናት ማእከል ማረጋገጡ የዜና ምንጩ ያመለክታል።

ከዚህ አዲሱ የትምህርት መርሃ ግብር ሌሎች የክርስትና ሃይማኖቶች ባለ መታከላቸው ምክንያት በትምህርቱ መርሃ ግብር ያልታከሉ ሃይማኖቶች ትችት እየቀረበ መሆኑ ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2009 የጋራ ሰነድ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ መወሰናቸውም ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.