2009-09-14 15:46:37

በፓኪስታን፣ ጸረ ክርስትያን አመጽ


ባለፈው ዓርብ በፓኪስታን ፑንጃብ መንደር ሙስሊሞች የዓርብ ጸሎት አድርሰው በመመለስ ላይ እያሉ በማበር ባንድ ክርስትያን ምእመን እና ባንዲት ሙስሊም መካከል የተፈጠረው ወዳጅነት እና ፍቅር በመቃወም RealAudioMP3 በክልሉ አቅራቢያ የሚገኘውን ቤተ ክርስትያን በእሳት ማጋየታቸው ሲገለጥ፣ በዚህች አገር አክራሪያን ሙስሊሞች በተከታታይ የሚፈጽሙት ጸረ ክርስትያን አመጽ ገና እንዳልተገታ ለማወቅ ተችልዋል። እክራሪያኑ በመቀጠል የአንዳንድ ክርስትያን ምእመናን መኖሪያ ቤቶች እና እንዲሁም የክልሉ የፕሮተስታን እና የካቶሊክ ምእመናን የጽሎት ቤቶችን በእሳት ማጋየታቸው የፓኪስታን የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትሕና የሰላም ድርገት ሊቀ መንበር አባ ኤማኑኤል ዩሳፍ ማኒ በመግለጥ፣ የፓኪስታን የሁሉም ሃይማኖቶች ምእመናን በጋራ ሰላማዊው የአብሮ መኖር ጉዳይ እንዲረጋገጥ እና ጸረ ክርስትያንም ይሁም ጸረ የማንም ዓይነት ሃይማኖት ምእመን እንዳይከሰት በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ያሰራጨው ዜና ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. ባለፈው ወር መግቢያ በጎጅራ ከተማ አሥራ አንድ ክርስትያኖች በአክራሪያን ሙስሊሞች ከተገደሉ ወዲህ፣ የክልሉ ነዋሪው ክርስትያን ማኅበርሰብ ቤቱን እና ንብረቱን እየተወ ለመፈናቀል አደጋ መጋለጡ እና በዚህ 2009 ዓ.ም. ውስጥ 9 ጊዜ ጸረ ክርስትያን እና አቢያተ ክርስትያን አመጽ መፈጸሙ አቨኒረ የተሰየመው የኢጣሊያው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ በመግለጥ ችግሩ ገና አሁንም እየቀጠለ መሆኑ ጋዜጣው ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.