2009-09-09 14:19:48

ግሪክ


ከኢራቅ ከኢራን እና ከባልካን ክልል አገሮች በተለያዩ ማኅብራዊ ሃይማኖታዊ ፖለቲካዊ ችግር ተገፋፍተው ወደ ግሪክ ለሚሰደዱት የቢዛንታይን ሥርዓት የሚከተሉት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን RealAudioMP3 ብግሪክ የቢዛንያይን ሥርዓት በምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ ሰብአዊ እና ማህብራዊ ድጋፍ እያገኙ መሆናቸው ተገለጠ።

የዚህ በግሪክ ያለችው የቢዛንይታይን ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቢተ ክርስትያን ምእመናን ብዛት ወደ 7 ሽሕ እንዲደርስ ማድረጉም ብፁዕ አቡነ ዲሞትሪዮስ ሳላካስ መግለጣቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ። በአቴንስ ለነዚህ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የቢዛንታይን ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን ካስተናገደቻቸው ቤተ ክርስትያን መፍነሳዊው ብቻ ሳይሆን ሰብአዊው ሕጽነት እና በተስተናገዱበት አገር ተዋህደው ለመኖር የሚያግዛቸው የባህል ሕንጸት ጭምር እያገኙ መሆናቸውም ብፁዕ አቡነ ሳላካስ ማስታወቃቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.