2009-09-09 14:18:18

ሰላም እንዲረጋገጥ ባንድነት መጾም እና መጸለይ


ባለፈው እሁድ ባፍሪካ ምዕራባዊ ኤኳቶር ሰላም እንዲረጋገጥ ሃይማኖታዊ ሁለ ገብ የእግር ጉዞ በሱዳን መከናወኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ። ይህ በጸሎት እና በጾም የተሸኘው የእግር ጉዞ RealAudioMP3 የተለያዩ ሃይማኖት ምእመናን ሰላም እና መረጋገት እንዲወርድ በማሰብ ከታምቡራ እስከ ያምቢዮ ከተማ 20 ኪሎ ሜትር ያጠቃለለ እንደነበር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።

የታምቡራ እና ያምቢዮ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ሂቦሮ ኩሳላ ይህ የክልሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ያነቃቃችው የሰላም የእግር ጎዞ ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ ህዝቡ በመተባበር ጸሎት እና ጾም እንዲያደርግ የተከናወነ መንፈሳዊ መርሃ ግብር የመጀመሪያ እንዳልሆነ ገልጠው፣ በዚህ ክልል ያለው ውጥረት እጅግ አሳሳቢ እንደሆነና በዚህ በሱዳን ደቡባዊው ክልል የጌታ ሰራዊት በማለት እራሱን በሚጠራው ያማጽያን ኃይል የሚያካሄደው የጦርነት ዘመቻ ከወዲሁ ካልተገታ የክልሉን ሰላም ከማናጋት አልፎ የብዙ እልቂት እና ጸአት ምክንያት እንደሚሆ ነው ካሉ በኋላም ሰላም የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነው ስለዚህ እያንዳንዱ ለሰላም ያለውን ፍላጎት በማነቃቃት የሰላም መሣሪያ ሆኖ እንዲገኝ ወደ እግዚአብሄር መመለስ ወሳኝ መሆኑ የሚያሳስብ መንፈሳዊ መርሃ ግብር መሆኑም ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.