2009-09-07 14:34:18

ጽንስ ማስወረድ የሞት ባህል ነው


በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የቦስቶን ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማለይ ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ የአሜሪካ የጤና ጥበቃ ጉዳይ ለማደስ የወጠኑት እቅድ ጽንስ ማስወረድን ለሚደረገው የሕክምና ስልት RealAudioMP3 ድጋፍ የሚሰጥ እንዳይሆን፣ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አመለካከት ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቴድ ኬኔዲይ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመሩበት ዕለት ባሰሙት ስብከት ገልጠዋል።

የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት የሕክምና አገልግሎት ኵላዊ ይሆን ዘንድ ዘወትር የሚያቀርቡት ጥሪ እና ከጤና ጥበቃ ጉዳይ የሚገለል ማንም የኅብረተሰብ ክፍል ሊኖር እንደማይገባው በተከታታይ ያቀረቡት ሀሳብ፣ ብፁዕ ካርዲናል ሲን ፓትሪክ ኦማለይ ዳግም ገልጠው ጽንስ የማስወረዱ ጸረ ሕይወት ተግባር የሚደገፍ መመሪያ ቤተ ክርስትያን መቼም ቢሆን ከመቃወም ወደ ኋላ እንደምታል ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.