2009-09-04 14:38:13

ኃይለኛ ዝናብ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በምዕራብ አፍርካ

 


የአፍሪካ ምዕራባዊ ክልል አገሮች ኃይለኛ ዝናብ ባስከትለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ መጠቃታቸው ተገለጠ። ይህ በቡርኪናፋሶ እና በኒጀር በስፋት በመታየት ላይ ያለው የተፈጥሮ አደጋ RealAudioMP3 ብዙ ሕዝብ ለመፈናቀል አደጋ ማጋለጡ እና በሰው ሕይወትም ላይ አደጋ ማስከተለ ይነገራል። የቡርኪናፋሶ መራሔ መንግሥት ተርቲዩስ ዞንጎ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ በኡጋዱጉ ክልል አምስት ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸውና 110 ሺሕ ህዝብ ንብረቱንና ቤቱን ጥሎ መፈናቀሉ በመጥቀስ ለተጎዳው ሕዝብ ድጋፍ ለመስጠት መንግሥታቸው የትብብርና የድጋፍ እቅድ መወጠኑም አስታውቀዋል።

በኒጀር ጭምር ተመሳሳይ ጉዳት እያስከተል መሆኑና በአጋደዝ ከተማ 3 ሺሕ እና 500 መኖሪያ ቤቶች መውደማቸው ሲታወቅ፣ የሴነጋል ለ ሶለይል የተሰኘው ዕለታዊ ጋዜጣ በአገሪቱ የሚታየው ሃይለኛው ዝናብ እስከ ፊታች ሰኞ ድረስ እንደሚቀጥል ያገሪቱ የስነ አየር ንብረት የጥናት ማእከል ማሳወቁ ሚስና የዜና አገልግሎት እንደገለጠውም፣ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.