2009-09-04 14:34:14

ለእረኞች እና ለማህበራዊ ጉዳይ መስተዳድሮች ትልቅ አብነት


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትላትና ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ትልቁ ጎርጎሪዮስ አክብራ ውላለች። ቅዱስ ጎርጎሪዮስ ትልቁ ር.ሊ.ጳ. እና የቤተ ክርስትያን ሊቅ ከሰሜን ኤውሮጳ የመጡ ኋላ ቀር RealAudioMP3 ህዝቦች ወረራ በፈጸመበት በስድስተስኛው ክፍለ ዘመን የኖረ ቤተ ክርስትያንን በእግዚአብሔር ጥበብ የመራ በግብረ ገብ ሕይወት የተካነ ለእረኞች እና ለማህበራዊ ጉዳይ መስተዳድሮች ትልቅ ኣብነት ነበር በማለት ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ ሁለቴ እሁድ ማርያማዊ ጸሎት ከመምራታቸው በፊት እና እንዲሁም የአንድ የረቡዓዊ አስተምህሮአቸው ዋና ርእስ በማድረግ እንደገለጡት ይታወሳል።

ጎርጎሪዮስ ገና በ 30 ዓመት እድሜው የሮማ የመንግሥት ኅየነተ በመሆን በማህበራዊ እና በመንግሥታዊ ሥራ ተጠምደው ሕይወታቸውን ሲመራ ቆይቶም ገዳማዊ ሆነው እግዚአብሔርን ሕዝበ እግዚአብሔርን እና በዘመኑ በሥቃይ ላይ ለነበረቸው ቤተ ክርስትያን በማገልገል ላይ እያለ ህዝበ እግዚአብሔር ለኚህ ታላቅ የቤተ ክርስትያን ልጅ የነበራቸውን ፍቅር መሠረትም ባንድ ድምጽ የእነተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያንን መሪ እንዲሆኑ የሰጠው ድጋፍ መሠረት ር.ሊ.ጳ. ሆነው እንዳገለገሉ እና ር.ሊ.ጳጳስነት ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስቶስ ምክትል፣ ማለትም አፈ ክርስቶስ የሚልት ትርጉም በመስጠት የእግዚአብሔር አገልጋዮች አገልጋይ በሚል አገላለጥ በመኖር የክርስቶስን ትህትና እና ጥበብን በማጉላት ቤተ ክርስትያንን የመራ ቅዱስ ነው።

የእግዚአብሔር አገልጋዮች በፍቅር ተገፋፍተው በአስተንትኖ እና በተግባር የተካነ እምነትን በጸሎት እና በሕይወት ለመኖር የተጠሩ፣ የሌሎችን ስቃይ እራስን ዝቅ አድርጎ መካፈል እና የራስ አድርጎ መኖር ፍጹም ወደ ሆነው እግዚአብሔር የምናደርገው ጉዞ መለኪያ መሆኑ በቃል እና በሕይወት የመሰከረ፣ የሮማዊው ባህል እና የባርባሪያን ባህል ግረጎሪዮስ ትልቁ የመሰከሩት በግብረ ገብ እጹብ ድንቅ ክርስትና ባህል አማካኝነት አዲስ ሥልጣኔ እንዲረጋገጥ ያደረጉ ናቸው በማለት ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ እ.ኤ.አ. መስከረም 3 ቀን 2006 ዓ.ም. መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ባሳረጉበት ወቅት በሰጡት አስተምህሮ እንደግለጡዋችውም ይዘከራል።

በእግዚአብሔር ፍቅር የተሞላ በእግዚአብሔር ውስጥ የሰጠመ በእግዚአብሔር ፍላጎት የተቃጠለ በዚህ ትልቅ መንፈሳዊነት መሠረትም ለሁሉም ለተናቁት እና ለተረሱት ቅርብ ለመሆን የበቃ ሰላምን ያነቃቃ ተስፋ እንዳይጨለም አብነት የሆነ የእውነተኛ ሰላም እና የተስፋ ምንጭ የሆነው ክርስቶስ በሕይወት እና በቃል የመሰከረ እንደነበርም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲስቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ሮቡዓዊ አስተምህሮ ማብራራታቸው ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.