2009-08-31 14:00:32

ያለፈው የታሪክ ሥህተት ዳግም እንዳይከሰት


ቅዱስ ኤጂዲዮ የኢጣሊያ የካቶሊክ ማኅበር እና በፖላንድ የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ድስዝዊች አነሳሽነት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 6 ቀን እስከ 8 ቀን የናዚው ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት RealAudioMP3 በሰው ዘር ላይ እልቂት የፈጸመበትን 70ኛው ዓመት ለመዘከር በአውሽዊዝ የእልቂት ሠፈር መፍነሳዊ ጉብኝት ይከናወናል።

በተጨመሪም ይህ እለት 20ኛው ዓመት የበርሊን ግንብ እና በኤውሮጳ የኮሚኒዝም ሥርዓት የወደቀበት 20ኛው ዓመት በጣምራ የሚዘከርበት ቀን ሲሆን፣ የሚከናወነው መንፈሳዊ ጉብኝት የታሪክ ክስተት እግምት ውስጥ በማስገባት የሚከናወን መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት ከሰጠው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል። ይህ መንፍሳዊ ጉብኝት የእርቅና የሰላም ምልክት እንዲሆን ታቅዶ የሚከናወን መሆኑም የጉብኝቱ አዘጋጆች ባሰራጩት መግለጫ እንዳመለከቱ የዜናው ምንጭ ጠቁሞ ይኸንን ታሪክ ማንኛውም አመጽ፣ እልቂት እና ጦርነት ለውጥረት ፈጽሞ መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል የሚመስከርበት ሲሆን፣ የቺፕሮ የኮስታሪካ የአልባኒያ፣ የቲሞር ኢስት፣ የፖላንድ እና የኡጋንድ መንግሥታት መሪዎች በሚካሄደው መንፈሳዊ ጉብኝት እንደሚሳተፉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.