2009-08-26 13:20:39

የሥርየተ ሐጢአት ሐዋርያዊ መንበር


ፒየትሮ ዳ ሞሮነ ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. 1294 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ለመሆን ተመርጠው ቸለስቲኖ አራተኛ የሚል መጠሪያ ስም የመረጡ የተወለዱበት 800ኛው ዓመት በአኵይላ ከተማ በተለያዩ መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብር RealAudioMP3 ተሸኝቶ እንደሚከበር ተገለጠ። አኩይላ ያብሩዞ ክፍለ ሃገር ከተማ ምንም’ኳ በቅርቡ በመሬት መናወጥ አደጋ የተጠቃች ብትሆንም የክፍለ ሃገሩ ሕዝብ በአሉን ለማክበር የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ተገልጠዋል።

የር.ሊ.ጳ. ቸለስቲኖ አራተኛ የተወለዱበት 800ኛው ዓመት ዓርብ ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. የቅስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ እንደሚከፈት ከቅድስት መንበር የተላለፈ መግለጫ ያመለክታል። ሐዋርያዊ መንበረ ንሥሐ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ስም ልዩ እና ሙሉ የሐጢአት ሥርየተ ማወጁ ሲገለጥ፣ እያንዳንዱ ምእመን እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ር.ሊ.ጳ. ቸለስቲኖ አራተኛ ትሩፋት በሚገኝበት ጸሎት ለሚያደርግ የሐጢአጥ ሙሉ ሥርየት እንደሚያገኝ ቅድስት መንበር አስታውቃለች። ምእመናን የዚህ ልዩ እና ሙሉ ሥርየተ ሐጢአት ተሳታፊ እንዲሆንም የር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ቸለስቲኖ አራተኛ ትሩፋት በአብሩዞ እና በሞሊሰ ክፍለ ሃገር ኡደት እንደሚያደርግ የሥርየተ ሐጢአት ሐዋርያዊ መንበር ያወጣው መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.