2009-08-26 13:24:59

ሶማሊያ


በሶማሊያ ያለው የዝናብ እጥረት እያስከተለው ባለው ድርቅ ሳቢያ 60 በመቶ የገጠር ነዋሪውን ሕዝብ እጅግ ለርሃብ ማጋለጡ የሶማሊያ መልሶ የማቋቋም ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አብዲሃኪም ጋራአድ ሞሓመድ እስታውቀዋል። RealAudioMP3 ተከስቶ ባለው የተፈጥሮ ችግር የተጠቃው የሕዝብ ብዛት በአኃዝ ዘርዝሮ ለማቅረብ የሚያዳግት ቢሆንም ቅሉ፣ ባደጋው ሳቢያ ወደ ተለያዩ የመጠለያ ማእከል የሚጎርፈው ህዝብ ብዛት እግምት ውስጥ በማስገባት በርሃብ የተጎዳው ህዝብ ብዛት ለመገመቱ ኣይዳግትም። ባለፉት ስድስት ወራቶች ውስጥ ከጠቅላላ የሶማሊያ ህዝብ ውስጥ ግማሹ በረሃብ አደጋ መጠቃቱ የተባበሩት መንግሥታት የሕዝቦች የምግብ ዋስት ብቃት የሚከታተለው ኮሚቴ ያሰራጨው መገልጫ የጠቀሰ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

በምግብ እጥረት ከሚሰቃየው የአገሪቱ ሕዝብ ውስጥ 75% በሶማሊያ ማእከላዊ እና ደቡባዊ ክልል የሚኖር መሆኑም የአለም አቀፍ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ሲያስታውቅ፣ በዚህ ክልል በምግብ እጥረት ለሚሰቃየው ሕዝብ እርዳታ ለማቅረብ በክልሉ ያለው ግጭት አቢይ እንቅፋት መሆኑም ሚስና የድርጅቱን መግለጫ በመጥቀስ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.