2009-08-26 13:23:53

ስደተኞች እና ኤውሮጳ


ትላትና ጧት አንዲት 57 የሕገ ወጥ ስደተኞችን ያሳፈረች አነስተኛ ባለ ሞተር ጀልባ ሲቺሊያ ከሚገኘው ከላምፔዱሳ የኢጣሊያ የባህር በር 30 ማይልስ ርቀት ላይ በሚገኘው በማልታ የባህር ክልል እያለች RealAudioMP3 በኢጣሊያ የባህር ድንበር አስከባሪ ኃይል እርዳታ አማካኝነት ካደጋ መትረፏ ተገለጠ።

የኢጣሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ፍራንኮ ፍራቲኒ ይኸንን ማኅበራዊ ክስተት የሆነው የሕገ ወጥ ስደተኞች ጉዳይ ኤውሮጳዊ ምላሽ የሚያሻው ነው እንዳሉም ሲገለጥ፣ ስለዚሁ ጉዳይ ኤወሮጳ የጋራ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት ያላት አይመስልም በማለት ወቀሳ የሰነዘሩ ሲሆን፣ ያም ሆኖ ይህ የኤውሮጳ ኅብረት ፓርላማ እ.ኤ.አ. መስከረም 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ስለዚህ ማኅበረሰብአዊ ክስተት ጉዳይ ለመወያየት ልዩ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተገልጠዋል።

በኢጣሊያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የካሪታስ የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ ስለ ስደተኞች እና ተፈንቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት ተጠሪ ኦሊቪየሮ ፎርቲ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሕገ ወጥ ስደተኞች ጸዓት ኢጣሊያ ማልታ ስፐይን እና ግሪክን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን በጠቅላላ ኤውሮጳ የሚመለከት እና ኤውሮጳዊ ምላሽ የሚያሻው ጉዳይ ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዱ አባል አገር በተናጥል ጸዓቱን ለመቆጣጣር ብቻ በሚል ግፊት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ የማያግዝ እያጸደቀው ያለው የስደተኛ ማስተዳዳሪያ ሕግ ጊዚያዊ እና የመተዳዳሪያ እና የወንጀለኛ መቅጫ ጠቅላይ በሕገ መንግሥት አንጻር ትርጉም የሌለው ማህበራዊ ኑሮ በቀስታ የሚያውክ ነው ስለዚህም ይኽ ስነ ሰብአዊ እና ስነ ማኅበረሰብአዊ ክስተት በሚገባ አጢኖ ተገቢ ምላሽ በመስጠት ክስተቱ የሚያስክተትለው የሰው ልጅ እልቂት ለማስወገድ ይቻላል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.