2009-08-24 14:30:56

የባርነት ሥርዓት ቢገረሰስም ከዓለማችን የባርነት ተግባር ግን ፈጽሞ አልተወገደም


የሰው ልጅ መሸጥ እና መለወጥ ሕግ በሰው ዘር በተለይ ደግሞ በጥቁር ያለም ማህበርሰብ ዘንድ ያስከተለው አሰቃቂው ግፍ የሚፈቅድ ሕግ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 22 እና 23 ቀን 1791 በሥርዓቱ ይጠቁ የነበሩት ያፍሪካ ህዝቦች RealAudioMP3 በሳን ዶሚንጎ ያነሳሱት አመጽ መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ ይህ ጸረ የባርነት ሥርዓት ንቅናቄ የተጀመረበት እለት በያመቱ የጸረ ባርነት እለት ሆኖ የሚዘከር ነው።

የባርነት ሥርዓት የተገረሰሰበት 200ኛው ዓመት ቢዘከርም ቅሉ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ለየት ባለ መልኩ እየተፈጸመ ነው። በዚህ ሥውር የባርነት ተግባርም በውስጥ አካል ንግድ፣ በሰው ጉልበት ብዝበዛ፣ ባመንዝራነት ህይወት አማካኝነት175 ሚሊዮን ህዝብ ለባርነት አደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ የስነ አፍርቃ ሊቅ ኣባ ጁሊዮ አልባነዘ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የባርነት ሥርዓት ሕጋዊ የሚያደርገው ውሳኔ ቢገረሰስም ቅሉ በዚህ በምንኖርበት ዘመን በተለያየ መልክ ሥውር ሆኖ እግብር ላይ ሲውል ይታያል ብለዋል።

በሕግ ይፈቅድ የነበረው የባርነት ሥርዓት የተካው የባርነት ተግባር በግድም በውድም እግብር ላይ ሲውል ይታያል፣ ሕዝቦች በከፋው ድኽነት ምክንያት የውስጥ ሰውነት አካል እስከ መሸጥ ያመንዝራነት ሕይወት እስከ መምረጥ ትምህርት እስከ ማቋረጥ በሥራ ዓለም መቀጠር የወንጀል ቡድኖች ለሚፈጽሙት ሰዎችን ከቦታ ቦታ የማንቀሳቀስ ሕገ ወጥ ተግባር ተጋልጠው እንደሚገኙም ጠቅሰው፣ የሰው ልጅ መብት እና ፈቃድ በማይከበርበት የተለያዩ ተግባሮች ገና ባለማችን እያንሰራፋ መሆኑ አስታውሰው፣ ለዚህ አዲስ የባርነት ተግባር ለመሳሰሉት ወቅታዊ ኢሰብአዊ ድርጊቶም የተጋለጡትን ሕዝቦች ከባንርነት ሥርዓት ነጻ ማላቀቅ የሁሉም መንግሥታት ተቀዳሚ ዓላማ መሆን ይገባዋል ብለዋል። ማርቲን ሉተር ኪንግ የሚያስፈራው የባርነት ሥርዓት ሳይሆን የቅን መሳይ ሰዎች ዝምታ ነው ያሉትን ህሳብ ዘክረው፣ በአሁኑ ወቅት የሰውል ልጅ ለተለያዩ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ያሚያጋልጡ ተግባሮች እያየህ ዝም ማለቱ ከባርነት ወንጀል የከፋ አቢይ ወንጀል መፈጸም ማለት ነው ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.