2009-08-21 14:10:23

የአፍጋኒስታን ሕዝባዊ ምርጫ ሂደት


በአፍጋኒስታን የመጀመሪያው ዴሞክራሲያዊ ሕዝባዊ ምርጫ ትላትና እግብር ላይ መዋሉ ተገለጠ፣ ያገሪቱ ርእሰ ብሔር እና 34 የክፍለ ሃገራት እንደ ራሴዎች ለመምረጥ ትላትና የተካሄደው ምርጫ የአገሪቱ የታሌባን አሸባሪያን ኃይሎች RealAudioMP3 ለማሰናከል ከምርጫው ቀነ ቀጠሮ በፊት እና ምርጫው በተካሄደበት ዕለትም የህዝቡን ተሳትፎ ለማሰናከል በመጠነ ሰፊ የሽበራ ጥቃት የተሸኘ እንደነበርም ታውቀዋል።

ስለ ተካሄደው ህዝባዊ ምርጫ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ባርባራ ስኪያቩሊ ከካቡል እንደዘገቡት የተካሄደው ምርጫ የተዋጣለት ነበር ባይባልም’ኳ በተረጋጋ ሁኔታ መከናወኑ ገልጠው፣ የታሊባን ዛቻ እና የሽበራ ጥቃት የህዝቡ ተሳትፎ እምብዛም እንዲጓደል አላደረገም ብለዋል። ያፍጋኒስታን ሕዝብ ከዚህ የከፋ ውጥርረት እና ብጥብጥ አሳልፈዋል፣ ስለዚህ በተካሄደው ምርጫ ለመሳተፍም የታሊባን ዛቻ አቢይ ግምት ቢሰጠውም ቅሉ ህዝቡ ለነዚህ አሸባሪያን ኃይሎች ያለው ጥላቻ በይፋ የገለጠበት ዴሞክራሲያዊ መድረክ እንደሆነም፣ ከመራጩ ህዝብ ያገኙትን አስተያየት እንዲህ ባለ መልኩ ገልጠዉ፣ የምርጫው ውጤት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በፊት ይፋ እንደማይሆን አስታውሰው፣ ይኸም የምርጫ ተቆጣጣሪ ኮሜት የምርጫው ሂደት በተመለከተ ግምገማ ከሰጠበት በኋላ እንደሚሆን ገልጠዋል።

ለዓለም አቀፍ የካቶሊክ ማህበረሰብ በአፍጋኒስታን ተጠሪ ኣባ ጁዜፐ ሞሬቲ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የአፍጋኒስታን ህዝብ አስተዋይ እና ችግር መከራ የፈተነው ገና ከዘርፈ ብዙ ጭግሮች ያልተላቀቀ ቢሆንም ቅሉ፣ ነበር የጣሊባን መንግሥትን ጨርሶ የማይመኝ መሆኑም አብራርተው፣ ለዚህ በጠና ድኽነት ለሚሰቃየው ያፍጋኒስታን ህዝብ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚቀርብለት የሰብአዊ እርዳታ በቂ እንዳልሆነም አባ ሞረቲ ጠቅሰው፣ የአፍጋኒስታን ረጂ አገሮች የገቡትን ቃል ሙሉ በሙሉ እግብር ላይ ባይውልም ህዝቡ ወደ ኋላ ለመመለስ እንደማይሻ የገለጠበት ሕዝባዊ ምርጫ ነበር ብለዋል። የአገሪቱ ወቅታዊው ሁኔታ እግምት ውስጥ በማስገባት የታሊባን መንግሥት የሚናፍቅ ሕዝብ በጣም ጥቂት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.