2009-08-21 14:14:50

ኢራን


የኢራን ርእሰ ብሔር አህመዲነጃድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ስም ዝርዝር በይፋ አስታወቁ። በሳቸው የሚመራው መንግሥት በኢራን እስላምዊት ሬፓብሊክ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ሴቶችን ያሳተፈ RealAudioMP3 21 ሚኒስትሮች እንደሚኖሩት ያሳወቁ ሲሆን፣ የአህመዲነጃድ መንግሥት እና በዚህች አገር የሴቶች ተሳትፎ ምን እንደሚመስል በኢጣሊያ የሚኖሩት አንዳንድ የኢራን ስደተኛ ዜጋ ሴቶች ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ርእሰ ብሔር አህመዲነጃድ ከመለመሉዋቸው 21 ሚኒስትሮች ውስጥ ሶስት ሴቶች እንዲሆኑ የመፈለጋቸው ዓላማ በሴቶች ተሳትፎ ላይ እምነት እንዳላቸው ለመመስከር ሳይሆን፣ ውጫዊ ውበት ለማስጠበቅ እርሱም በምዕራቡ ዓለም ተቀባይነት እንደሌላቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸው ምክንያት፣ የሚከተሉት ያገር ውስጥ እና የውጭ ፖሊቲካ በማተካከል ሳይሆን ሴቶችን በማሳተፍ ብቻ ተቀባይነት እንዲኖራቸው አቅደው የወሰዱት ውሳኔ ነው። ያም ሆኖ ይኽ የኢራን መንግሥት ሚኒስትሮች ያገሪቱ መንፈሳዊ የበላይ መሪ ውሳኔ የሚከተሉ የሚጠብቁ እና እግብር ላይ የሚያውሉ በመሆናቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማንም ብትመርጥ ለውጥ የለው፣ በኢራን የሚያስፈልገው መሠረታው ለውጥ መሆኑ ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.