2009-08-19 13:43:49

የአፍጋኒስታን ሕዝባዊ ምርጫ ሂደት


በአፍጋኒስታን የሚካሄደው ህዝባዊ ምርጫ እግብር ላይ ለማዋል አንድ ቀን ቀርቶት ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአገሪቱ የታሌባን ኃይሎች የጥቃት ዛቻ ከፍ እያለ መምጣቱ ተገለጠ፣ ያሸባሪያኑ ቡንድ በተለያዩ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች RealAudioMP3 ክልል ጥቃት እንደሚጥል በማሳሰብ ህዝቡ ለምርጫ ባይወጣ ይሻላል የሚል ተበራሪ የፖሮፓጋንዳ ጽሑፎች ባፍጋኒስታን እየበተኑ መሆናቸውም ይነገራል።

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ሕዝባዊ ምርጫ እንደሚካሄድ ሕዝባዊ ምርጫውን ለማሰናከል ዓማጽያን የታሌባን ኃይሎች የሰነዘሩት የጥቃት ዛቻ እግበር ላይ እያዋሉት ሲሆን፣ ትላንትና ጧት በአገሪቱ ርእሰ ብሔር ሕንጻ እና በአፍጋኒስታን የጸጥታ ኃይሎች ጠቅላይ ሠፈር ኢላማ ያደረገ ጥቃት መጣሉ እና ቀጥሎም የካቡል መሃል ከተማ በፍንዳታ አደጋ ያናወጡ ሁለት ባፍጋኒስታን ለተባበሩት መንግሥታት ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የአገሪቱ ዜጎች የሚገኙባቸው ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ ሌሎች ከሃምሳ በላይ የሚገመቱት ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋ።

ሕዝባዊ ምርጫውን ለማሰናከል አማጽያን የታሊባን ኃይሎች በተለያዩ ያገሪቱ ክልሎች መጠነ ሰፊ ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን፣ በካቡል አንዲት ቦምብ የተጠበምደባት ተሽከርካሪ መኪና አንዲት የሰሜን ቃል ኪዳን የመከላከያ ኃይል አባላት ያሳፈረች የወታደራዊ መኪና ጋር መጋጨቷ ሲነገር በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ አለ መኖሩ ተገልጠዋል። አንድ አሸባሪ ባጥፍተህ ጥፋ ሴራ አማካኝነት አራት ያፍጋኒስታን የመከላከያ ህይል አባላትን ለሞት መዳረጉ ተገልጠዋል። በራፋህ አውራጃ በኢሳፍ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ጋር የተሰማሩት የኢጣሊያ ወታደሮች ከአፍጋኒስታ የመከላከያ ኃይል አባላት ጋር በመሆን በክልሉን ጸጥታ ለማስከበር በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው ሲነገር ይህ በንዲህ እንዳለም በራፋህ ሰሜናዊ ክልል አንድ ጥቃት ለመሰንዘር በመዘጋጀት ላይ የነበረ የአሸባሪያን ቡድን በኢጣሊያ የመከላከያ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጠዋል።

በጠቅላላ ባፍጋኒስታን ያለው ሁኔታ እጅግ የተወጠረ መሆኑ ሲገለጥ፣ በአገሪቱ ያለው ጸጥታ እና ደህንነትም ኮሳሳ መሆኑ ይነገራል፣ የሚካሄደው ህዝባዊ ምርጫ እንዳይሰናከል በአፍጋኒስታን የሚገኘው የኢሳፍ የመከላከያ ኃይል አባላት ከአገሪቱ የመከላከያ ኃይል አባላት ጋር በጣምራ ጸጥታ እና ደኅንነት ለማስከበር ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ በስፋት መሠማራታቸው ከካቡል የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.