2009-08-17 14:31:50

የዋና ጸሓፊ ክሊንተን ያፍርካ ጉብኝት መጠናቀቅ


የተባበሩት ያሜሪካ መግንሥታት ዋና ጸሃፊ ሂላሪ ክሊንተን በተለያዩ ሰባት የአፍሪካ አገሮች ያካሄዱት ይፋዊ ጉብኝት ከትላትና በስትያ መጠናቀቁ ተገለጠ። ሂላርይ ክሊንተን በአፍሪካ አገሮች የዲሞከራሲ ሥርዓት RealAudioMP3 የሚያረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ ፖሊቲካዊ ተሃድሶ ወሳኝ መሆኑ በዚህ የአፍሪካ ይፋዊ ጉብኝታቸው አበክረው ያቀረቡት ጥሪ መሆኑ ሲነገር፣ በኢጣሊያ ቶሪኖ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የስነ አፍሪካ እና የአፍሪካ ስነ መዋቅር ታሪክ መምህር የታሪክ ሊቅ አና ቦኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ብቻ ሳይሆን ሌሎች የተለያዩ የአፍሪካ ረጂ አገሮች ለአፍርካ እድገት እና ልማት ያቀና ትብብር በተለያዩ ዘርፎች ደገፍ የሚቀርብ ቢሆንም ቅሉ ከዚህ ቀደም ድጋፉም ይሁን እርዳታው ከአፍሪካ ምንም ነገር ሳይጠበቅ ለአፍሪካ እርባና ይቀርብ ነበር፣ አሁን ግን የድጋፉ መመዘኛ የአፍሪካ አገሮች ሙስና አድልዎ ለማስወገድ የሚያደርጉት ጥረት እና የሰው ልጅ መብትና ፈቃድ ጥበቃ እግብር ላይ ለማዋል የሚከተሉት የፖለቲካ ሥራዓት እንዲሁም ለዲሞክራሲ መረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት መሆኑ ገልጠው፣ አንዳንድ አገሮች የአፍሪካ ፖለቲካዊ መታደስ ወሳኝ መሆኑ እያወቁ ነገር ግን የአፍሪካ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መታደስ እንደመመዘኛ ሳይመለከቱ፣ የኤኮኖሚ ጥቅማቸው ላይ ብቻ በሚያተኩር ለአፍሪካ የኤኮኖሚ ልማት በሚል ሽፋን የተሰማሩ አገሮች እንዳሉ አስታውቀው፣ የአፍሪካ ፖለቲካዊ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ መሻሻል መሠረት ያደረገ የትብብር እና የድጋፍ እቅድ እጅግ ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.