2009-08-17 14:29:13

የአፍርካ የተረሱ ግጭቶች


በአፍሪካ በሚካሄዱት ግጭቶች ሳቢያ በጠቅላላ በየዓመቱ 3000 ሺሕ ህዝብ ለሞት እንደሚዳረግ ሲገለጥ፣ የአፍሪካ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብም ይሁን በመንግሥታትም ጭምር የተዘነጋ እና ግድ የማይሰጠው ሆኖ፣ RealAudioMP3 በስነ ፖለቲካ በስነ መገናኛ ብዙኃን መድረክ የተረሱ ግጭቶች ተብለው እንደሚገለጡም የሚታወቅ ነው። ፕሮፈሶር ጃምፓውሎ ክላኪ ኖቫቲ ፓቪያ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የአፍሮ አሲያቲክ - የስነ አፍሪካ እና የስነ እስያ መምህር ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በብዛት የአፍሪካ ግጭቶች በተፈጥሮ ጸጋ የታደሉት ክልሎች ለመቆጣጠር ታልሞ የሚቀሰቀሱ መሆናቸው አውስተው፣ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲላቀቁ የሸኘው ያገር ወዳድነት መንፍስ እንዲሁም ነጻ በወጡበት ማግሥት የነበረው ያገር ፍቅፍ ስሜት የላቀና አሳድሮት የነበረውን አገርን ለመገንባት ሕዝብን ለማነጽ ዓቢያ ፖሊቲካዊ ማኅበራዊ ፍላጎት እየዳሸቀ በሥልጣን ላይ የወጣው መንግሥት ሥልጣን ለሕዝብ የሚለው ውሳኔ ወደ ጎን በማድረግ፣ ሥልጣኑን ለማራዘም የሚከተለው ፖለቲካዊ ሥርዓት አንዱ የግጭቶች መንስኤ መሆኑ ገልጠው፣ የቅኝ ግዛቱ የተወገደ ቢሆንም ቅሉ ህዝቡ በገዛ የአገሪቱ መንግሥት ዳግም ይገዛዋል፣ ይህ ደግሞ ለተለያዩ ሽምቅ ተዋጊዎች የነጻነት ግንባር ታጣቂ ኃይሎች መወለድ ምክንያት ሆኖ የትጥቅ ትግል ያነሳሳል። የአንዳንድ የአፍሪቃ አገሮች የመልካም ምድር አቀማመጥ እና ያላቸው የተፈጥሮ ሃብት ለበለጸጉ አገሮች ፖሊቲካዊ ኤኮኖሚያዊ መስህቦ በመሆኑም ምክንያት በቀጥታ በነዚህ ሃብታም አገሮች ፍላጎት ምክንያት የሚቀሰቀሱ ግጭቶችም እንዳሉ አብራርተዋል።

ስለዚህ የአፍሪካ እና የእስያ አገሮች ግጭቶች የተወሳሰበ በመሆን በፖለቲካው መድረክ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚነካም ስለ ሆነ፣ መፍትሄው ግልጽ ቢሆንም ቅሉ እግብር ላይ ማዋሉ ግን በጣም ያዳግታል። የአፍሪካ ግጭቶች መፍትሔ እንዲያገኙ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጸመው የሰላም አስከባሪ ተልእኮ ሚና ሥውር ዓላማ ያለው ይመስላል፣ ምክንያቱም በስተጀርባው ጥቅምን የማስጠበቅ እቅድ ያለው ተልእኮ ነውና። የሰውን ሕይወት ማእከል የሚያደርግ የፖለቲካ ሥርዓት የሰላም ተልእኮ ለአፍሪካ ሰላም ወሳኝ ነው በማለተ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.