2009-08-17 14:27:56

የብጹዕ አቡነ ኦስካር አርኑልፎ ሮመሮ ዝክረ ሰማዕትነት


በላቲን አሜሪካ የሳልቫዶር ካቶሊክ ቤተክርስትያን የሳን ሳልቫዶር ሊቀ ጳጳሳት የነበሩት የብፁዕ አቡነ ኦስካር አርኑልፎ ሮመሮ የተገደሉበት 30ኛው ዓመት ለመዘከር በመዘጋጀት ላይ መሆኗ ተገለጠ። RealAudioMP3 ብፁዕ አቡነ ሮመሮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 24 ቀን 1980 ዓ.ም. መስዋዕተ ቅዳሴ በማቅረብ ላይ እያሉ መሣሪያ በታጠቁ ሰዎች እጅ መገደላቸው የሚዘከር ሲሆን፣ የክልሉ ህብዝ 30ኛው ዓመት ዝክረ ሰማዕትነት ብፁዕ ኣቡነ ሮመሮ በሚከበርበት የቅዳሴ ስነ ሥርዓት የጓተማላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሮዶልፎ ኵዌዛዳ እና ብፁዕ አቡአ ሮመሮ ቅዱስ ተብለው በቤተክርስትያን እንዲታወጅላቸው ቅድመ ጥናት እና ሂደቱን የሚከታተሉት በኢጣሊያ የተርኒ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያ ይሳተፉ ዘንድ ጥሪ አቀርበዋል።

ዛሬ ብፁዕ አቡነ ሮመሮ ከተገደሉባት ቤተ ክርስትያን ተነስቶ እስከ ቁምስና ኩስካትላን መንፈሳዊ ንግደት መከናወኑ እና መንፈሳዊው ንግደቱም እዛው በቁምስና ኩስካትላን ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ተፈጽመዋል። እስከ መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀድመው ያሉት ስድስት ወራቶች በተለያዩ ስለ የእግዚኣብሔር አገልጋይ ብፁዕ አቡነ ሮመሮ ታሪክ፣ መፍነሳዊነት እና እረኛነት ጉዳይ በተመለከተ ቲዮሎጊያዊ ውይይቶችና ዓውደ ጥናቶች እንደሚካሄዱ ሲገለጥ፣ ብፁዕ አቡነ ሮመሮ ድምጽ ለሌላውቸው በጠና በድኽነት በጭቆና ለሚሰቃዩት ለተናቁት ለተገለሉት ሁሉ ድምጽ ነበሩ በማለት የላቲን አሜሪካ የቤተ ክርስትያን የታሪክ ማህደር ይገልጣቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.