2009-08-14 16:34:26

የኤስያ ጳጳሳት ምክር ቤት አጠቃላይ ጉባኤ


የኤስያ ጳጳሳት ምክር ቤት አጠቃላይ ጉባኤ ዋና ጸሓፊ የኮታባቶ ፊሊፒንስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኦርላንዶ ቢ ኰቨዶ፣ ‘‘የክርስትና ሃይማኖት በኤስያ መታደስ ያስፈልገዋል፣ እንዲሁም ከተለያዩ ባህሎች ሃይማኖቶችና የአህቡሩ ሕዝብ መወያየት የምትችል ኡውነትኛ ቤተ ክርስትያን መታነጽ አለበት’’ ሲሉ 9ኛ የኤስያ ጳጳሳት ምክር ቤት አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ከፍተዋል። ጉባኤ እአአ ብ1975 የተመሠረተ ነው፣ በአሁኑ ጊዜ 23 አገሮችን በሚወክሉ 137 አባላት የቆመ ነው።

እአአ በ2004 ዓም በኮርያ ስለ ቤተ ሰብ ካደረጉት ጉባኤ፣ ጳጳሳቱ ዘንድሮ ለ6 ቀናት በማኒላ የፊሊፒንስ ዋና ከተማ እስከ 16 ነሐሴ ‘‘የቅዱስ ቍርባን ሕይወት በኤስያ’’ በሚል ርእስ 9ኛውን አጠቃላይ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

አሽያ ኒውስ የተባለ የዜና አገልግሎት እንዳመለከተው፤ የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ልዩ መልእክተኛ በመሆን ልሂቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንሲስ አሪንዘ እአአ ነሐሴ 10 ቀን 2009 ዓም ጉባኤውን በቅዳሴ ከፈቱት። ብፁዕነታቸው በስብከታቸው የጉባኤውን ርእስ አስመልክተው ይዘቱ የአህጉሩ ቤተ ክርስትያን መጪውን ሕይወት ይወስናል’’ ብለዋል።

ብፁዕ ኣቡነ ቀቨዶ በመክፈቻው ንግግራቸው የአስያ ቤተ ክርስትያን ተልእኮ ገልጸዋል። ከዓለማችን ሕዝብ 60 በመቶ በአሽያ ኣህጉር ይኖራል። ይህ ሕዝብ ቃለ እግዚአብሔርን ከእኛ ይጠብቃል። በብዙ የአሽያ ቦታዎች ድምጸ አልባ የእምነት ምስክርነት የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማስፋት የሚያገለግል ብቸኛው ዘዴ ነው ሲሉ የአህጉሩ ምእመናንና ቤተ ክህነት ይህንን አብነት በመከተል ለአዲስ ስብከተ ወንጌል እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል። ይህንን ተልእኮ እውን ለማድረግና የአህጉሩን ቤተ ክርስትያን በአዲስ መንፈስ ለማነጽ የወጣቶችና የድህቾን ፍላጎት በማጥናትና መልስ በመስጠት ለእምነትና ለተልእኮ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ሲሉ የጉባኤ ተሳታፊዎችን ተማጥነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.